ለትግራይ ክልል በአለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል አስፈላጊ የህክምና መድሃኒቶችን የማድረሱ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው
የኢትዮጵያ መንግስት ከሚሰራቸው ቀዳሚ ተግበራት መካከል የጤና አገልግትን ለሁሉም ዜጎች ማድረስ አንደኛው ሲሆን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስትም እያንዳንዱ ዜጋ የጤና አገልግሎት የማግኘት ጉዳይን በግልጽ ተጠቅሷል፡፡
ስለሆነም ዜጎች የጤና አገልግሎት በፍትኃዊነት የማግኘት መብት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የፖሊሲ አቅጣጫዎች በኢፊዲሪ የጤና ፖሊሲ ተካተዋል፡፡
ከዚህ አኳያ በአገራችን በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ዜጎች የጤና አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብዓዊና ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዳይስተጓጎሉ የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለጤና አገልግሎት አስላፈጊ የሆኑ ድጋፎችን የማድረስ ተግበራትን አከናውኗል፣ እያከናወነም ይገኛል፡፡