Articles

የጤና ሚኒስቴር ''አሻራችን ለትውልዳችን፣ አረንጓዴ ተክላችን ለጤንነታችን!" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል ተከናወነ።

Dr. Lia Tadesse

በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት (በገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል) የተከናወነ ሲሆን በ2014 ዓ.ም ክረምት ወራት የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት  ከ50 ሺ በላይ ችግኞችን ለመትከል ወደ ተግባር መግባቱን የጤና ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።


በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት (በገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል 20  ሺህ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች የመትከሉ መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን በተጨማሪም በማእከሉ የተከናወኑ የልማት እና የማስፋፊያ ስራዎች የወተት ልማትን ጨምሮ የከተማ ግብርናን የመተግበር ስራ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ተጎብኝተዋል። ይህም ተግባር በማዕከሉ ያለውን የምግብ አቅርቦት በራስ አቅም ለመሸፈን ያስችላል ተብለዋል።

የሚሊኒየም ኮቪድ ህክምና እና ድንገተኛ ምላሽ ማዕከል የምስጋና እና የማስረከብ ፕሮግራም ተከናወነ

የሚሊኒየም ኮቪድ ህክምና እና ድንገተኛ ምላሽ ማዕከል

የጤና ሚኒስቴር ላለፉት ሁለት ዓመታት የኮቪድ የህክምና እና የድንገተኛ ምላሽ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አዲስ ፓርክ /የሚሊኒየም አዳራሽ/ ከምስጋና ጋር ለሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስረከበ።


የጤና ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ማዕከሉን ለሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ባለፉት ሁለት ዓመታት የኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል ብዙ ውጣ ውረዶች ማለፋቸውን ጠቅሰው ዛሬም ኮቪድ እያስከተለ ያለው ችግር ባይቆምም ለዚህ ዕለት በመብቃታችንና የሚሊኒየም የህክምና ማዕከልን መልሰን ማስረከብ በመቻላችን ደስተኞች ነን ብለዋል።

የቤተሠብ እቅድ አገልግሎትን ለማስፋፋት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የድርሻቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ ገለፁ። 

House of Representatives

ይህ የተገለፀው የጤና ሚኒስቴር በቤተሠብ እቅድ አገልግሎት ተደራሽነት፣ ስኬት እና ክፍተት በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባደረገው የግንዛቤ መስጨበጫ መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ እንዳሉት የቤተሠብ እቅድ አገልግሎት መስጠት የሴቶች እና ህጻናት ህይወት ለመታደግ ዋነኛው አቅጣጫ መሆኑን ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ጠቅሰው ይህን አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረት ተሠጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ ገልጸዋል።


ባለፉት አመታት በቤተሠብ እቅድ አገልግሎት የተሠሩ ሥራዎች እና የተገኙ መሻሻሎች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም 22 በመቶ የሚሆኑ በለትዳር ሴቶች አገልግሎቱን ለማግኘት ቢፈልጉም ተደራሽ ማድረግ አለመቻሉን የገለጹት ሚኒስትር ድኤታው ይህም በበጀት አመቱ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት መሆኑም አስረድተዋል።