የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ማህበር 7ኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ጉባኤ ተካሄደ
በእለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የኢትዮጵያ ጤና ፖሊሲ በማህበረሰብ ጤና ማጎልበት፣ በሽታ መከላከልና የጤና አገልግሎት ሽፋን ማሻሻል ላይ ትኩረት አደርጎ የተሰራበት እና በዚህም ብዙ ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደነበር የተናገሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን የተላላፊ በሽታዎች ብቻ ሳይሆኑ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና አደጋዎችም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን ተከትሎ የከፍተኛ የፈውስ ህክምና ፍላጎትም እንዲሁ የጨመረበት ወቅት በመሆኑ የጤና ሚኒስቴር ለዚሁ ምላሽ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የሶስተኛ ደረጃ /tertiary care/ አገልግሎት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማሻሻል እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡