ኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ግሎባል ዋን ሄልዝ ፕሮግራም በሰሜኑ ክፍል በነበረው ጦረነት ለተጎዱ የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረገ
በዛሬው እለት የተደረገው ድጋፍ 9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የላብራቶሪ እቃዎች መሆናቸው ማወቅ የተቻለ ሲሆኑ ድጋፉ የተደረገው በአማራ እና በአፋር በክልል ለሚገኙ ስድስት ሆስፒታሎች ሲሆን በስድስቱ ሆስፒታሎች ውስጥ ላሉ የላብራቶሪ ክፍሎችን መልሶ ለማደረጃት የሚረዳ ድጋፍ ነው፡፡
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት በአገራቱ የነበረው ጦርነት የጤና ተቋማትን ማውደሙን ተከትሎ መልሶ ለማቋቋም በተደረገው ርብርብ ሁሉም ሆስፒታሎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን አንስተዋል፡፡ ኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ግሎባል ዋን ሄልዝ ፕሮግራም ለዚህ ችግር ትኩረት በመስጠት የሆስፒታሎችን ላብራቶሪዎች ሙሉ ለሙሉ ለመደገፍ መቻሉን ዶክተር ሊያ የተናገሩ ሲሆን በቴክኒክም የማጠናከር ስራ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡