100 የልብ ህሙማን ህጻናት ነጻ ህክምናና የአየር ትኬት ወጪ በመሸፈን በህንድ ሀገር ለማሳከም እንዲሁም በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የሚሰጠዉን እገለገሎት በዘላቂነት ለማጠናከር ሁለት የመግባቢያ ሰነዶች ተፈረመ።
የ100 የልብ ህሙማን ህጻናት ህክምናና የአየር ቲኬት ሙሉ ወጪ በመሸፈን ህንድ ሃገር ለማሳከም የመግባቢያ ሰነድ በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትጵያ አየር መንገድ፣ በሮታሪ ኢንተርናሽናል እና በኢትጵያ ልብ ህሙማን ማህበር የተፈረመ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የሚሰራውን ስራ የሚያጠናክር የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡
በመንግስት ተቋማትና በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ብቻ ከ7,000 በላይ ህጻናት ለልብ ቀዶ ህክምና ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ የተናገሩት ዶ/ር ሊያ፤ እነዚህን ችግሮች ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዛሬ ሁለት የመግባቢያ ሰነዱች እንደተፈረሙ ገልጸዋል፡፡