በጤና ኤክስቴንሽን መርሃ-ግብር ትግበራ የአጋር ድርጅቶች ሚና ውጤታማ ነበር
በጤና ኤክስቴንሽን መርሃ-ግብር ትግበራ በርካታ የጤና አገልግሎቶች ማህበረሰቡን ተደራሸ ለማድረግ የአጋር ድርጅቶች ሚና ውጤታማ እንደነበር እና እንደ ሃገር አመርቂ የጤና ውጤቶች የተመዘገበበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ እንደገለጹት የጤና ስርዓታችን በተለይም የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎትና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነበት የጄ ኤስ አይ/ኤል10ኬ 10 ኪሎ ሜትር/JSI L10K 10K/ ባለፉት 14 ዓመታት የነበረው አገልግሎት ውጤታማ እንደነበር አንስተው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት በመስራት ለተገኘው ውጤትና ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው። በቀጣይም ይህ ፕሮጅክት ቀጣይነት እንዲኖረው ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት በትብብር ውጤታማ ስራ ለመስራት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡