በሀገራችን ያለውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር የሚያችል አውደ ጥናት ተካሄደ
በቅርቡ የታተመው የላንሴት ግሎባል የጤና ኮሚሽን ሪፖርት ላይ በማተኮር "የህብረተሰብ ጤና ክብካቤ ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ሰውን ማስቀደም" በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ፋይናንስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶችን በማካተት አውደ ጥናት አካሄዷል፡፡
በአገራችን በሽታን በመካከልና ጤና ማበልጸግ ፖሊሲን በመቅረጽ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ዘዴን ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝና የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ማሻሻያ ፍኖተ ካርታንም በመዘርጋት ሞዴል ወረዳዎችን ለመፍጠር፣ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሸፋንን ለማሳደግ እና ሁሉንም የጤና ተቋማት ወደ ከፍተኛ አፈጻጸም ለመቀየር በመላ ሀገሪቱ እየተሰራበት እንደሚገኝ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡