“በጎነት ለጤናችን’’በሚል ነፃ የጤና ምርመራ እና የህክምና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ሳምንት ከመቶ ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የነጻ የጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግለት ለመስጠት የተጀመረው ሰው- ተኮር የበጎ ፈቃድ የተግባር ዘመቻ በሁሉም ክልሎችና በከተማ መስተዳደሮች በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል፡፡
በዘመቻውም የጤና አጠባበቅ ትምህርትና ምክር አገልግሎት ፣ በተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣የኮሌራና ሌሎች ውሀ ወለድ በሽታዎች፣ ወባ፣ ኤች አይ ቪ ፣ ቲቪ ፣ ኮቪድ-19፣ የካንሰር ህመምና ሌሎች ትኩረት በሚሹ የጤና ጉዳዮች ላይ ማለትም የደም ግፊት ፣የደም የስኳር መጠን፣ ከአንገት በላይ፣ የአይን፣ የቆዳ፣የስነ ምግብ፣ የአእምሮ ጤና እና ሌሎች የጤና አገልግሎቶች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡