በኢትዮጵያ በአዲስ ቴክኖሎጂ ህክምና የሚሰጥ የመጀመሪያው የስትሮክ ህክምና ማእከል በዛሬው እለት ተመርቆ ተከፍቷል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሠ በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንዳሉት የጤናው ዘርፍ በርካታ መሻሻሎች እያሣየ ያለ ቢሆንም ገና ብዙ ወደ ፊት መሄድ ይጠበቅበታል ብለዋል። የአክሶል ስትሮክ እና ስፓይን ማእከል መከፈቱ እንደ ሀገር የእስትሮክ ህክምናን አንድ ምእራፍ ወደ ፊት የሚወስድ መሆኑን ጠቅሰው ማእከሉ ለዚህ ምረቃ በመድረሱ ያላቸውን አድንናቆት ገልጸዋል። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ እና የተለየ አገልግሎት ይዞ የመጣ ማእከል በአገሪቱ መከፈት መቻሉ ለጤናው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
ላለፋት አመታት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና በዚህ ሳቢያ የሚመጣ ሞት እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ዶክተር ሊያ ይህን ችግር ለመቅረፍ የጤና ሚኒስቴር ከመከላከል ስራው ጎን ለጎን የስፔሻሊቲ ህክምና አገልገግሎት ማስፋፋት ስራ የሚያሰራ የአስር አመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ እየተተገበረ መሆኑን አስረድተዋል።