የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጄኤስአይ ዋና ስራ አስፈጻሚና ፕሬዝደንት ጋር ተወያዩ
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጄኤስአይ ዋና ስራ አስፈጻሚና ፕሬዝደንት ማርጋሪት ክሮቲ እና የጂኤስአይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ተደርገው አዲስ የተሾሙት ዶ/ር ቢኒያም ደስታ ጋር ተወያዩ ።
የጄኤስአይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር መሰየሙ በጤና ሚኒስቴር እና ጄኤስአይ መሃል ያለውን ትብብር እና ግንኙነት እንደሚያጠናክር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በውይይታቸው የገለጹ ሲሆን፤ ጄኤስአይ የጤና ሚኒስቴር ጠንካራ አጋር መሆኑን እና ጤና ሚኒስቴር አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡