Articles

ኢትዮጵያ ጤናማና አምራች የሆነች አፍርካ እንዲኖረን ከአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር  በትብብር መስራቷንና እያደረገች ያለዉን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች-የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

Dr Mekdes Daba

ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል። 


በታንዛኒያ አቅራቢነት የተወዳደሩት ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ አባል አገራት በሰጡት ድምጽ አብላጫ በማግኘት ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል። 


የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት እንዲመሩ በመሰየማቸዉ እንኳን ደስ ያሎት ብለዋቸዋል።  

የማህበረሰብ አስተያየት መመዘኛ ስርዓትን ለማጠናከር እና የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያስችል ልምድ ልውውጥ እየተካሄደ ነው

community score card

ጤና ሚኒስቴር በጤና ተቋማት የሚሰጡ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል የማህበረሰብ አስተያየት መመዘኛ ካርድ (community Score Card) እየተገበረ ሲሆን በዚህ የአተገባበር ስርዓት ዙርያ ኢትዮጵያ ያላትን አሰራርና ልምድ ለማካፈል ብሎም በጋና ሀገር ያለውን የማህበረሰብ አስተያየት መመዘኛ ስርዓት ትግበራ ተሞክሮ ለመቅሰም ከተለያዩ የስራ ክፍሎችና ክልሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ቡድን በጋና ሀገር ልምድ ልዉዉጥ እያደረገ ይገኛል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በድሬዳዋ  አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ወረዳ በሠቆጣ ቃልክዳን፣ የስርአተ ምግብ አተገባበር እና በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የተሠሩ ስራዎች ጎበኙ

Dre Dawa

በጉብኝቱ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ የምግብና የስርአተ ምግብ ስትራቴጂን አተገባበር የተጎበኘ ሲሆን የሰቆጣ ቃልክዳን በስምምነቱ መሰረት በመተግበር በርካታ እፃናት ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም  ተገልጿል። 

በሌማት ቱሩፋት  እና የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በተወሰዱ እርምጃዎችም የቢዮ አዋሌ ነዋሪዎች ተጠቃሚ  በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገብ መቻሉ ተነስቷል። 

ከጉብኝቱ በተጨማሪም የችግኝ ተከላ መርሃግብርም ተከናውኗል።