Articles

የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች አስቸኳይ ህክምና እና የካሳ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ

የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጅዎች የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ 799/2005 ዓ.ም በጸደቀው መሰረት በሁሉም ጤና ተቋማት እስከ ሁለት ሺህ ብር አገልግሎት በነፃ እንዲያገኙ ተደንግጓል፡፡ ይህንም አዋጅ መሰረት በማድረግ በተሻሻለው በደንብ ቁጥር 554/2016 የድንገተኛ ህክምና ወጪ እስከ አስራ አምስት ሺህ ብር እንዲሻሻል የተደረገ ሲሆን ለዚህም እረቂቅ መመሪያ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ተዘጋጅቷል፡፡

በእረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 05/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡

መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ  ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ ትሰራለች፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ 

Dr. Mekdes Daba

በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገለጸዋል።


በመድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ዙሪያ ለመምከር በተዘጋጀው የከፍተኛ ሃላፊዎች መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ተጽእኖ ለመቀነስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራና ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ አስፋላጊውን ክትትል ማድረግና የምርምር ስራዎችን እንደምታጠናክር ገልጸዋል።  ይህ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስተሯ አስምረውበታል።

ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል እና መቆጣጠር ለስመዘገበችዉ አመርቂ ዉጤት እዉቅና አገኘች

Dr Mekdes Daba

አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማት አበርክቷል።

እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ላስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA77) ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን ተቀብለዋል።