Articles

በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ  የደሴና የኮምቦልቻ ጤና ተቋማት በአሸባሪውና ወራሪው የህውሃት ቡድን አገልግሎት እንዳይሰጡ ሆነው ወድመዋል፡፡      

health facility

በደሴ ከተማ የሚገኘው የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሸባሪውና ወራሪው የህውሀት ቡድን አገልግሎት እንዳይሰጥ ሆኖ የወደመ ሲሆን ቡድን በተደራጀ መልኩ የህክምና መሳሪያዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ጭኖ ከመውሰዱ ባለፈ የቀሩትንም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አድርጎ ሙሉ በሙሉ አውድሟቸዋል።


ከእነዚህም መካከል በተኝቶ ህክምና፣ በፅኑ ህክምናና በአንስተኛና በከፍተኛ የቀዶ ህክምና ክፍሎች የነበሩ በብዙ ሚሊዮን ብር የተገዙ የትንፋሽ መስጫ /ventilator/ እና አንስቴዥያ ማሽኖች የተወሰዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በመውደማቸው በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል።

የጤና ሚኒስቴር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 30 ሚሊዮን ብር እና 1.5 ሚልዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የዓይነት ድጋፎችን አደረገ

donation

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ  እንደተናገሩት አሁን ላይ አገራችን እና ህዝቦቿ ከመቼውም በተለየ ከውስጥም ከውጪም ፈተናዎች  እና መሰናክሎች የገጠሟት ወቅት ላይ እንደምንገኝ ገልጸው በሁሉም መስኮች በማህበራዊ ፣ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በውጭ ጉዳዮቻን ላይ የገጠሙን ችግሮች ለጊዜው ሊፈትኑን እና ሊከብዱን ቢችሉም እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ እነዚህ ዓይነት መሰል ውስብስብና ከባድ ችግሮች ሲገጥሙን ይህ የመጀመርያችን አይደለም፤ ቀደም ሲል ከውስጥም ከውጭም  ችግሮች የገጠሙን ወቅት በነበረን አገራዊና ህዝባዊ  ፍቅር፣ በነበረን መደማመጥና መግባባት፣ ሚሊዮኖች እንደ አንድ ሆነን፣  አንዱ እንደሚሊዮን ሆኖ ችግሮቹን እና ፈተናዎችን ተሻግረን  ዛሬ ላይ መድረሳችን በቂ ማሳያ ነው ሲሉ የአንድነት ጥንካሬያችንን አስታውሰዋል::

የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ ሊካሄድ ነው!

covid19

ጤና ሚኒስቴር ከመምህራት ማህበር ጋር በመሆን የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ ውጤታማ በሚሆንበት  መንገድ ዙሪያ በአዳማ እየመከረ ነው፡፡  


የፀጥታ ችግር በሌለባቸው የአገራችን ክፍሎች ከ12 ሚሊዮን በላይ ዶዝ ለመከተብ የታሰብ ሲሆን በተለይም በትምህርት ቤት እና በዩኒቨርስቲዎች ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የጤና ሚኒስቴር የክትባት ባለሙያ አቶ ተመስገን ለማ ተናግረዋል፡፡


በክትባት ዘመቻው እድሚያቸው ከ18 አመት በላይ የሆነ ማንኛው ሰው እና በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን የመከተብ ስራ እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልፃል፡፡


ከኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ በተጨማሪ በቀጣይም የማህፀን በር ካንሰር ክትባት በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች እድሚያቸው ከ14 አመት ለሆናቸው ልጃገራዶች ክትባቱን ለመስጠት የዘመቻ ስራ እንደሚጀመር አቶ ተመስገን ለማ ጠቁመዋል፡፡