ጤና ሚኒስቴር ለአማራ ክልል ለወደሙ የጤና ተቋማት አጋር አካላትን በማስተባበር ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የህክክምና ግብአቶችን፣ መድሀኒቶችን፣ አንቡላንሶችን እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አስረከበ።
የጤናማ እናትነት ወር በደሴ ከተማ በተከበረበት ስነስርአት ጤና ሚኒስቴር አጋር አካላትን በማስተባበር ለእናቶች እና ህጻናት ጤና ከፍተኛ እገዛ ማድረግ የሚችሉ ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ግብአቶችን፣ መድሀኒቶችን፣ ሁለት አንቡላንሶችን እና ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ወራሪው ሀይል ተቋሞቻችንን ቢያወድምም ጠንካራ መንፈሳችንን እና ህብረታችንን ከቶ ሊሰብር አይቻለውምና ከቀድሞ በበለጠ እጅ ለእጅ ያተያይዘን ተቋሞቻችንን እንገነባለን ሲሉ ተናግረዋል።