በጦርነት እና በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነ አዕምሮ እና የስነ ልቦና ህክምና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በጤና ሚኒስቴርና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የተዘጋጀ የዘርፈ ብዙ ምላሽ እቅድ ይፋ ተደረገ
በተለያዩ ክልሎች በጦርነት እና በተፈጠሩ ግጭቶች ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተቀናጀ የስነ አዕምሮ እና የስነ ልቦና ህክምና ምላሽ በመስጠት እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ይበልጥ ለማጠናከርና ፈጣን ለማድረግ የጤና ሚኒስቴር እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት እቅድ ለባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያ የህረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች የመልሶ ማቋቋምና ሪዚሊየንስ ዳይሬክተር በሆኑት በዶ/ር ያረጋል ፉፋ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በቅንጅታዊ ርብርቡ የስነ አዕምሮ ፣ የስነ ልቦና እና የማህበራዊ ስራዎች እንዲሁም ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር ተግባራት እንደሚከናወኑ በእቅዱ የተካተቱ ዝርዝር አላማዎች ያሳያሉ፡፡