ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድን አገልግሎት ተደራሽ ላልሆኑ የአርብቶ አደር የህብረተሰብ ክፍሎች
ከጥቅምት 19_21/2014 ዓ.ም በሶማል ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚካሄደው የጤናው ዘርፍ ልማት የምክክር ጉባኤ በመጀመሪያ ቀን ውሎ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ተሞክሮዎችን ምልከታ በማድረግ ጀምሯል።
በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ሀዋ ሱሌማን የተመራው ቡድን ከጅግጅጋ ከተማ 55 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ጎልጃኖ ወረዳ መልካዳ ካስ ቀበሌ የመስክ ጉብኝት አካሂዷል።
በጉብኝቱም ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው የተንቀሳቃሽ የጤና ቡድን አገልግሎት የስራ ተሞክሮ ታይቷል። በሶማሌ ክልል በ29 ቡድኖች የተንቀሳቃሽ የጤና አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን እያንዳንዱ ቡድን ለስድስት ቀበሌዎች አገልግሎት ይሰጣል።