በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው 23ኛ የጤናው ዘርፍ ጉባኤ ተሳታፊ የነበሩ ሁሉም ታዳሚዎች የኮቪድ 19 ምርመራ እንደተደረገላቸው ተገለጸ።
ይህም በርካታ ቁጥር ያለው ተሳታፊ ለሚገኝባቸው ወሳኝ ሀገራዊ ሁነቶች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መሆኑ ተነግሯል።
"ፈጣን ምላሽ ሰጪ የጤና ስርአት በአዲስ ምእራፍ" በሚል መሪ ቃል የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መዲና በሆነችው ጅግጅጋ ሲካሄድ የሰነበተው የጤናው ዘርፍ ጉባኤ ሁሉም ተሳታፊዎች ከጉባኤው አንድ ቀን አስቀድሞ የኮቪድ 19 ምርመራ የወሰዱበትና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ተሳታፊዎች የተገኙበት እንዲሁም ሌሎችም ሁሉም የጥንቃቄ መንገዶች የተተገበሩበት እንደሆነ ገልጸው ለሌሎች ተመሳሳይ ሀገራዊ ሁነቶች ትምህርት የሰጠ እንደነበር ተሳታፊዎች ተናግረዋል።