የጤና ሚኒስቴር በአለታ ወንዶ ከተማ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አባወራዎች ያስገነባቸው ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረከበ
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በክረምት በጎ አገልግሎት በአለታ ወንዶ ከተማ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ስድስት አባወራዎች/እማወራዎች ያስገነባቸውን ቤቶች ለተጠቃሚዎች ያስረከቡ ሲሆን በክረምት በጎ አገልግሎት የጤና ሚኒስቴር ችግኞችን የመትከል እና አቅመ ደካሞችን የማገዝ ስራን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው በአለታ ወንዶ ከተማም ምሳሌ መሆን የሚችል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። ቤቶቹም መሰረታዊ መገልገያ ቁሳቁስ የተሟላላቸው ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ግለሰቦችም በሰጡት አስተያየት መጠለያ ማጣት እጅግ አስቸጋሪ ህይወት እንዲመሩ እንደዳረጋቸው ሆኖም ጤና ሚኒስቴር እንደደረሰላቸው እና ተስፋቸውን እንዳለመለመ ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።