የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን እና የአገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጅማ ከተማ የሚገኘው የጅማ ዩኒቪርሲቲ ሆስፒታልን የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን፣ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአስተዳደር ህንጻ ጎብኝተዋል፡፡ ህንጻው ከፍተኛ አቅም ያለው የዳታ ሴንተርን አካቶ የተገነባና በቀጣዩ አመት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡
የሆስፒታሉ የካንሰር ማእከል፣ የምርምር ላብራቶሪ፣ የጽኑ ህሙማን፣ እና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችንም ዶ/ር መቅደስ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው የኬሞ እና የጨረር የካንሰር ህክምና፣ የቃጠሎ ፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ፣ የአካል ጉዳት እና የድንገተኛ አደጋ ህክምና፣ እንዲሁም የማህጸን እና ጽንስ እና የህጻናት ህክምና ክፍሎች እየሰጡ የሚገኘውን አገልግሎት መጎብኘት ተችሏል፡፡