የእናቶች ፣ ሕፃናት ጤና እና አፍላወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ

maternal

የእናቶች ፣ ሕፃናት  እና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ በሚኒስቴር ዴኤታ ጽ / ቤት ስር ከሚገኙ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች አንዱ ነው፡፡

የእናቶች ፣ ሕፃናት እና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ በስሩ

  • የስነ ተዋልዶ፣ የቤተሰብ ዕቅድ እና ወጣቶች ጤና
  • የእናቶች ጤና
  • የጨቅላ ህጻናት እና ሕፃናት ጤና       
  • የክትባት አገልግሎት ጤና ዴስኮችን ያቀፈ ሲሆን፤ በድምሩ 91 ሠራተኞችንም ይዟል፡፡

የእናቶች ፣ ሕፃናት  እና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች መሪ ስራ አስፈፃሚ ጋር፣ በአገሪቱ ካሉ ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያቤቶች እንዲሁም ከአገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበትና በመቀናጀት  ይሠራል ፡፡

መሪ ስራ አስፈፃሚው በተጨማሪም በመላ አገሪቱ ያሉ የስነተዋልዶ፣ የእናቶች ፣ የሕፃናትእና አፍላ ወጣቶች ጤና እና የክትባት ጉዳዮችን የሚመለከቱ ዋና ዋና መርሃ-ግብሮችን በመቅረጽና በመተግበር እንዲሁም በማስተግበር ለሚኒስቴሩ ተልዕኮ እና ራዕይ አስተዋፅዖ ያደርጋል ፡፡

በአጠቃላይ የእናቶች ፣ ሕፃናት  እና አፍላ ወጣቶች ጤና  መሪ ስራ አስፈፃሚ  ስር ያሉ ፕሮግራሞች  ጠቋሚ መርሆዎች

  • የአገር ባለቤትነት ፣ አመራርና ተጠያቂነት
  • ፍትሃዊነት እና ተደራሽነት
  • የማህበረሰብ ተሳትፎ ፣አቅም ግንባታ እና ባለቤትነት 
  • ቅንጅታዊ አሰራር
  • አጋርነት
  • ሀብቶችን በአግባቡ መጠቀም
  • ፈጠራ እና የቴክኖሎጅ  አጠቃቀም ማሳደግ
  • ምላሽ ሰጪነት
  • በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥ
  • ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ናቸው፡፡

የእናቶች ፣ ሕፃናት  እናአፍላ ወጣቶች መሪ ስራ አስፈፃሚ  ሚናዎችና ኃላፊነቶች

  • በአፋላ ወጣቶችና እና ወጣቶች ጤና ፣ ቤተሰብ ዕቅድ ፣ እናቶች ጤና ፣ በጨቅላ ህጻናት እና የሕፃናት ጤና ፣ እና ክትባት ኢኒሼቲቮችና ተግባራት ላይ መመሪያወችን በተዋረድ እንዲፈጽሙ ማድረግ፡፡
  • ለክልሎች እና ለጤና ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
  • ከክልሎች እና ተቋማት ለሚነሱ የእናቶች ፣ ሕፃናት ጤና እና ስነተዋልዶ ጤና ጋር ለተያያዙ መሳሪያዎች ፣ አቅርቦቶች እና ግብዓቶች  መልስ መስጠት
  • የእናቶች ፣ ሕፃናት እና አፍላ ወጣቶች ጤና ተግባራትን በተመለከተ ከሌሎች መንግስታዊ ድርጅቶች እና ሚኒስትሮች ጋር በትብብር እና በአጋርነት መስራት
  • ለእናቶች ፣ ሕፃናት እና አፍላ ወጣቶች ጤና ተስማሚ የሆኑ ፖሊሲዎች እና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ተግባራት እንዲቀረጹ ሃሳብ ማቅረብና መሟገት
  • ለእናቶች ፣ ሕፃናት እና አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስርዓተ ምግብ ስራዎች ሃብት ማሰባሰብ
  • ከልማት አጋሮች ፣ የሁለትዮሽ እና የብዙ ወገን ድርጅቶች ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ሲቪል ማህበራት ጋር መከላከል በምንችለው  የእናቶች ፣ ጨቅላ ህጻናት እና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ  በአጋርነት መስራት
  • መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ፣ የሙያ ማህበራት እና ማህበራት የቀረቡትን የእናቶች ፣ ሕፃናት እና አፍላ ወጣቶች ጤና ተግባራት አግባብነት ያላቸውን የፕሮጀክት ሀሳቦች ይገመግማል ፤ ምላሽ ይሰጣል፡፡
  • ከሃገር አቀፍ እቅዱ አንጻር ድጋፋዊ ጉብኝት ፣ ክትትል እና የአፈጻጸም ግምገማ ማድረግ
  • ለደንበኞች / ለአገልግሎት ተጠቃሚዎች ፍላጎቶች እና ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት
  • የስራ አስፈጻሚውን እቅዶች በጋራ ለመስራት እና ለመተግበር ለሚፈልጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተገቢውን መረጃ መስጠት