ብሔራዊ የወባ ማስወገጃ ፕሮግራም (NMEP)

malaria

ብሔራዊ የወባ ማስወገጃ ፕሮግራም(NMEP) በበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ስር ከሚገኙት ፕሮግራሞች መካከል በአንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ከወባ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ጣልቃ ገብነቶችን እና እንቅስቃሴዎችን የመንደፍ፣የማቀድ ፣ የመተግበር ፣ የመከታተል እና የመገምገም ኃላፊነት አለበት።

 

የ NMEP ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

  • የፀረ ወባ ጣልቃ ገብነቶችን መንደፍ ፣
  • የቴክኒክ መመሪያዎች፣ ማኑዋሎች ፣ፕሮቶኮሎች ፣መደበኛ የአሰራር ሂደቶች፣ እና የፈንድ ፕሮፖዛሎችን ማዘጋጀት እንዲሁም የንዑስ-ብሄራዊ የፕሮግራም ክፍሎችንና የሠራተኞችን አቅም መገንባት።
  • የፀረ ወባ መድሐኒቶችን እና የፀረ-ተባይ ውጤታማነት ከምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር መከታተል
  • የጣልቃ -ገብነት ተፅእኖን መለካት

 

ፕሮግራሞች ፣ ፕሮጄክቶች እና ተነሳሽነት

NMEP የአምስት ዓመት ብሔራዊ ስትራቴጂክ ዕቅድ (2021-2025) ያወጣ ሲሆን ዋናው አላማው ወባን ለመቆጣጠር በተደረገው ፍልሚያ የተገኙትን ድሎች ማጠናከር፣ የበሽታውን ሸክም የበለጠ መቀነስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የወባን ስርጭትን ማቋረጥ ነው። ሁለት ግቦች አሉት፡

  • በ 2025 የወባ በሽታን እና ሞትን በ2020 ከነበረው መነሻ ቁጥር በ50 ፐርሰንት መቀነስ።
  • በ 2025 ዓመታዊ የ ወባ ፓራሳይት ቁጥር ከ 10 በታች በሆኑ አካባቢዎች ውስጥ ዜሮ ሀገር ወለድ  የወባ በሽታን ማሳካት እና ዜሮ ሀገር ወለድ የወባ በሽታዎችን ሪፖርት በሚያደርጉ አካባቢዎች ውስጥ እንደገና የወባ በሽታ እንዳይከሰት መከላከል።

ፕሮግራሙ በ 2017 ንዑስ-አገራዊ የወባ በሽታን ማስወገድ ያስጀመረ ሲሆን የማስወገድ ፕሮግራሙን በሀገሪቱ በማስፋፋት ዜሮ ሀገር ወለድ የወባ አካባቢዎችን በ 2030 ለማስፋፋት አቅዷል።  በዚህም መሰረት አዲስ ጣልቃ ገብነቶች እንደ የወባ ታማሚ ማሳወቂያ፣ ምርመራ፣ ምደባ እና ምላሽ እና ወባ ተኮር ምርመራ ፣ ምደባ እና ምላሽ በቅርቡ ተጀምሯል።

 

የፕሮግራም ምዕራፍ

  • በ 2025 ወባ ስር በሰደደበት አካባቢዎች የሚኖሩ 85% ቤቶች የወባ መከላከያ ጣልቃ ገብነቶች ላይ ተገቢ ባህሪ እና ልምዶችን እንዲያዳብሩ ማድረግ።
  • በ2021 እና ከዚያ በኋላ በተጠረጠሩ የወባ ታማሚዎች የ100% ማረጋገጫ ምርመራ ማካሄድ እና በብሔራዊ መመሪያዎች መሠረት ሁሉንም የተረጋገጡ ታማሚዎች ማከም።
  • በ 2021 እና ከዚያ በኋላ ለወባ በሽታ ተጋላጭ የሆነን ህዝብ 100% በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚመከር አንድ አይነት የቬክተር ቁጥጥር ጣልቃ ገብነትን በመጠቀም መጠበቅ።
  • በ 2021 እና ከዚያ በኋላ በአሁኑ ጊዜ API ከ10 በታች በሆኑ አካባቢዎች ውስጥ የትኩረት ምርመራን ፣ ምደባን እና ምላሾችን ማካሄድና ዜሮ ሀገር ወለድ የወባ በሽታዎችን ሪፖርት የሚያደርጉ አካባቢዎች ውስጥ ወባ እንደገና እንዳይከሰት መከላከል።
  • በ 2021 እና ከዚያ በኋላ ተገቢ የውሳኔ አሰጣጥን የሚያመቻች 100% ማስረጃ ማቅረብ።
  • በ 2021 እና ከዚያ በኋላ ወባን የማስወገድ ጣልቃ ገብነቶችን ለማስተባበር እና ለመተግበር የሁሉም ደረጃ ጤና ቢሮዎችን  አቅም መገንባት።