መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ ትሰራለች፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ
በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገለጸዋል።
በመድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ዙሪያ ለመምከር በተዘጋጀው የከፍተኛ ሃላፊዎች መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ተጽእኖ ለመቀነስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራና ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ አስፋላጊውን ክትትል ማድረግና የምርምር ስራዎችን እንደምታጠናክር ገልጸዋል። ይህ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስተሯ አስምረውበታል።