የህክምና አገልግሎት መስጫ መሳርያዎች ማደሻና ማሻሻያ ማዕከል ግንባታ መጀመር የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
ጤና ሚኒስቴር ከኮሪያው ሪፐብሊክ ዓለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ ፋውንዴሽን (ኮፊ) ጋር በመተባበር የህክምና አገልግሎት መስጫ መሳርያዎች ማደሻና ማሻሻያ ማዕከል ግንባታ መጀመር የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የቆየ ወዳጅነት ያላቸው፣ በክፉና ደግ ጊዜያትም በአብሮነታቸው የጸኑ ሀገራት ናቸው ያሉት ዶ/ር መቅደስ ይህንን ሃገራዊ የህክምና መገልገያ እቃዎች ማደሻና ማሻሻያ ማዕከል ከደቡብ ኮሪያ መንግስት ጋር ስንጀምረው በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ከመተማመናችንም በላይ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት እና ትስስር የበለጠ እያጠናከርንም ጭምር ነው ብለዋል።