Articles

"ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ ክትባቶችን በቁጥርም በአይነትም በመጨመር የአገልግሎቱ ተደራሽነት እየሰፋ ነዉ" ዶ/ር ሊያ ታደሰ

Dr lia tadesse

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ያለበትን ሁኔታና በኮቪድ-19 ክትባት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሀገራችን የወረሽኙ ምጣኔ በአንፃራዊ ሁኔታ ከነበረበት የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሯ ካለፉት 3 ሳምንታት ጀምሮ ግን በሳምንታዊ ሪፖርት በበሽታው የመያዝ መጠን በ 4 እጥፍ ጭማሪ፣ በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች በ2.5 እጥፍ ጭማሪ፣ ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖች ደግሞ በ2.8 እጥፍ ጭማሪ ማሳየቱንና ይህም አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀዋል።  


ነገር ግን በሀገራችን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች ትግበራ እየቀነሰ በመምጣቱ በሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እየተከሰተ ያለው ሦስተኛ ዙር የኮቪድ-19 በሽታ የስርጭት ማእበል ችግር በኢትዮጵያ እንዳይመጣ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡