የ2016 ዓ ም የጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ አድራጎት ትግበራ ''በጎነት ለጤናችን"  በሚል መሪ ቃል ከፍለው መታከም ለማይችሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ  ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነጻ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት ለመሰጠት በማቀድ የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል

  • Time to read less than 1 minute
Dr Mekdes Daba

በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት የ2016 ዓ.ም የነጻ ጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ ማስጀመርያ መርሀ ግብር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም የህክምና ኮሌጅ  እና በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የተጀመረ ሲሆን ሌሎች ባለድርሻ አካላትንም በማስተባበር ሙሉውን ክረምት ሲከናወን የሚቆይ ይሆናል። 

የጤና ሚኒስትር ዶክተር  መቅደስስ ዳባ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት የዘንድሮው ነጻ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት  ከፍለው መታከም የማይችሉ ዜጎችን ለማገዝ እንደሚረዳና ንቅናቄውም ''በጎነት ለጤናችን"  በሚል መሪ ሀሳብ በአገር አቀፍ ደረጃ በስፋት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

በዘንድሮው የጤና ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ እንቅስቃሴም ከቀደሙት መርሀ ግብር በተለየ በየጤና ተቋማት ብልሽት ገጥሟቸው አገልግሎት የማይሰጡ የህክምና መስጫ መሳርያዎችን የመጠገን ተግባር እንደዚሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ለህክምና የሚያገለግሉ ዕጽዋትን የመትከል የመትከል መርሃ ግብር የሚያጠቃልል መሆኑን ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

የበጎ  ፍቃድ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር በተጨማሪ  የበርካታ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም  አካላት የድርሻውን እንዲወጡ በመጠየቅ አሁንም  እያደረጉት ላለው  ተሳትፎ  ሚኒስትራ ምስጋና አቅርበዋል።  ህብረተሰቡም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በመሆን የጤና ቅድመ ምርመራና ህክምና እንድያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ህክምና ኮሌጅ ዋና ፕሮቦስት ዶክተር ሲሳይ ስርጉ በበኩላቸው ሆስፒታሉ 30 አይነት ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን ያስታወቁ ሲሆን የቤት እድሳት፣ የችግኝ ተከላ ፣የአካባቢ ጽዳት፣ የመማርያ ቁሳቁስ ድጋፍ በመርሀግብሩ የተካተቱ ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኤካ ኮተቤ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሙሉ ቀን ተስፋዬ
ሆስፒታሉ ከየከ ክፍለከተማ  እና የግል የጤና ተቋማት ጋር በመተባበር 50 ሺህ የህብረተሠብ ክፍሎች ነጻ የጤና ምርመራ  እና የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ  እንደሚደረግ ገልጸዋል።በክፍለከተማው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተስብ ክፍሎችም የቤት እድሳት ለማከናወን መርሃ ግብሩ በይፋ ተጀምሯል።

ከብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የክረምት የበጎ  ፍቃድ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር በተጨማሪ  የበርካታ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም አካላት የድርሻውን እንዲወጣ በመጠየቅ ህብረተሰቡም እንደ ዋነኛ ድርሻ አካል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በመሆን የጤና ቅድመ ምርመራና ህክምና እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበው  በጎ ተግባር  መሳካት ዋነኛ አካል ለሆኑት የጤና ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል።