Articles

ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብን መፍጠር ለሰላም መረጋገጥ የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ ነው።

75th Annual World Health Summit

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ "ሰላም ለጤና ጤና ለሰላም!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው 75ኛው አመታዊ የአለም  ጤና ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብን መፍጠር መቻል አስተማማኝና ዘለቄታዊ ያለው ሰላም እንዲኖር ከማድረግ አንጻር ያላው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።


ያለሰላም የተሟላ ጤናም መኖር አይችልም ያሉት ሚኒስትሯ  በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት በርካታ የጤና ተቋማት እንደወደሙና እንደተዘረፉ በዚህም በርካታ ቁጥር ያለው ህብረተሰብ የተሟላ የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ መስተጓጓሉን ጠቅሰው የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የጤና አገልግሎትን ወደነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ75 ኛው የአለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው።

World Health Assembly

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በአካል የመጀመሪያ የሆነው ይህ የጤና ጉባኤ ግንቦት 14, 2014 ዓ.ም  በጄኔቫ ዝዊዘርላንድ በይፋ ተጀምሯል። 


"ሰላም ለጤና ጤና ለሰላም!"( "Peace for Health and Health for peace!") በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው 75 ኛው የአለም ጤና ጉባኤ ላይ የአለማችን የማህበረሰብ ጤና  አሁናዊና ቀጣይ  ስትራቴጅክ ጉዳዮች ቀርበው ምክክርና ውይይት የሚደረግ ሲሆን ጉባኤው ለአንድ ሳምንት በጄኔቫ የሚቀጥል ይሆናል።

በሀገራችን ያለውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር የሚያችል አውደ ጥናት ተካሄደ 

basic health care financial system

በቅርቡ የታተመው የላንሴት ግሎባል የጤና ኮሚሽን ሪፖርት ላይ በማተኮር "የህብረተሰብ ጤና ክብካቤ ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ሰውን ማስቀደም" በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ፋይናንስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶችን በማካተት አውደ ጥናት አካሄዷል፡፡


በአገራችን በሽታን በመካከልና ጤና ማበልጸግ ፖሊሲን በመቅረጽ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ዘዴን ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝና የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ማሻሻያ ፍኖተ ካርታንም በመዘርጋት ሞዴል ወረዳዎችን ለመፍጠር፣ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሸፋንን ለማሳደግ እና ሁሉንም የጤና ተቋማት ወደ ከፍተኛ አፈጻጸም ለመቀየር በመላ ሀገሪቱ እየተሰራበት እንደሚገኝ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡