Articles

በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ፕሮጀክት ባለፉት ስድስት አመታት ከ58 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት አግኝተዋል።

Dr. Lia Tadesse

የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ፕሮጀክት በማስተባበር ፓዝፋይንደር ከአሜሪካ እና ከኮሪያ ህዝብና መንግስት በሚደረግለት ድጋፍ ባለፉት ስድስት አመታት በስድስት ክልሎችና በ451 ወረዳዎች ፕሮጀክቶችን ሲሰራ መቆየቱን ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከዩኤስኤአይዲ ትራንስፎርም  ፕኤችሲዩ ጋር በመተባበር በመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልል ጤና ቢሮዎችና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጥራት ያለው የስነ ተዋልዶ፣ የእናቶች፣ የጨቅላ ህፃናት፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች እንዲሁም የስነ ምግብ አገልግሎቶች ተግባራዊ መደረጋቸው ዶ/ር ሊያ ታደሰ አንስተዋል፡፡

ዲጂታላይዝድ የታካሚዎች የጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ ‹‹ዌልነስ ፓስ›› የሙከራ ትግበራ ስምምነት ተፈረመ

Welfare Pass

የጤና ሚኒስቴር መተግበሪያውን  ወደ ስራ ለማስገባት ከማስተር ካርድ፣ ከጋቪ እና ከጄ ኤስ አይ ጋር ዛሬ ስምምነት ተፈራርሟል። 


የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በሁለተኛው የጤናው ዘርፍ እቅድ ውስጥ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ  አሰጣጥ ስርዓት ለማጠናከር ጥራት ያለው መረጃ ማሰባሰብ፣ መተንተን እና መጠቀም ቁልፍ ተግባራት አድርጎ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በዚሁ ወቅት ዲጅታል መተግበሪያው በሙከራ ደረጃ መጀመሩ በጤናው ዘርፍ ያለውን የመረጃ ስርዓት ለማዘመን እንደሚረዳ ገልፀዋል።


የታካሚዎችን የጤና መረጃ ስርዓት ፍሰትን ለማቀላጠፍ ማስተር ካርድ ‹‹ዌልነስ ፓስ›› የተባለው የዲጅታል መላ የሙከራ ትግበራውም በተመረጡ የጤና ተቋማት በ15 ወራት ውስጥ ለአንድ ሚሊዮን ተገልጋዮች ለማዳረስ የታለመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ 

100 የልብ ህሙማን ህጻናት ነጻ ህክምናና የአየር ትኬት ወጪ በመሸፈን በህንድ ሀገር ለማሳከም እንዲሁም በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የሚሰጠዉን እገለገሎት በዘላቂነት ለማጠናከር ሁለት የመግባቢያ ሰነዶች ተፈረመ።

memorandums

የ100 የልብ ህሙማን ህጻናት ህክምናና የአየር ቲኬት ሙሉ ወጪ በመሸፈን ህንድ ሃገር ለማሳከም የመግባቢያ ሰነድ በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትጵያ አየር መንገድ፣ በሮታሪ ኢንተርናሽናል እና በኢትጵያ ልብ ህሙማን ማህበር የተፈረመ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የሚሰራውን ስራ የሚያጠናክር የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

በመንግስት ተቋማትና በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ብቻ ከ7,000 በላይ ህጻናት ለልብ ቀዶ ህክምና ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ የተናገሩት ዶ/ር ሊያ፤ እነዚህን ችግሮች ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዛሬ ሁለት የመግባቢያ ሰነዱች እንደተፈረሙ ገልጸዋል፡፡