በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጋምቤላ ክልል የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ተጀመረ
በ2014 በጀት ዓመት በጤና ሚኒስቴር አስተባ ባሪነት ተጠሪ ተቋማትን ባከተተ መንገድ የተለያዩ የክረምት በጎፍቃድ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ዛሬ በጋምቤላ ከተማ፣ የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳትን አስጀመሩ። በዚህም የ 5 አቅመ ደካሞች ቤት ሙሉ በሙሉ የሚታደስ ይሆናል።
በክልሉ የአቅመ ደካማ ወገኖችንን ቤት ከማደስ ፕሮግራም ማስጀመር በተጨማሪ የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ፣ በክልሉ የሚገነባው ሪጅናል ላብራቶሪ ግንባታ ሒደት፣ እንዲሁም አሻራችን ለትውልዳችን በሚል መሪ መልክት በጋምቤላ ከተማ ጤና ጣቢያ የችግኝ ተከላ ተካሒዷል።
በመርሀ ግብሩም በክልሉ በዝቅተኛ ገቢ ከሚተዳደሩ የአቅመ ደካማ ልጆች ለ400 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ድጋፍ ተደርጓል።