Articles

"ድህረ ጦርነትና የአጥንት ህክምና" በሚል መሪ ቃል 16ኛ የኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና ሃኪሞች ማህበር አመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ

Dr. Ayele Teshome

በጉባዔው ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ የማህበሩ አባላት በግለሰብም ደረጃም ሆነ እንደ ተቋም ሃገር በተቸገረችበት ጊዜ ሁሉ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች በተለይም በጦርነት ጉዳት ለሚደርስባቸው የኢትዮጵያ ጀግና ሰራዊት አባላትን ህይወት ለመታደግ ላበረከቱት እና እያበረከቱት ያለው አገልግሎት በታሪክ መዝገብ ላይ መፃፉን ጠቅሰው ለአበርክቶዓቸው ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች ብለዋል።

እኤአ በ2030 የቲቢ በሽታን ለመግታት ቀጣይነት ባለዉ የልማት ግብ የተያዘዉ ዕቅድን ለማሳካት ተገቢዉን ትኩረት ሳያገኝ የቆየዉ የህጻናትና አፍላ ወጣቶች የቲቢ በሽታ ልይታ፣ ምርመራና ህክምና ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት  ያስፈልጋል።

Dr. Lia Tadesse

የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በሎሜ ቶጎ እየተካሄደ ባለዉ 72 ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እንደገለጹት በኢትዮጵያ በ2015 የጸደቀዉ የህጻናትና አፍላ ወጣቶች የቲቢ በሽታ ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ ህጻናትና አፍላ ወጣቶችን ከቲቢ በሽታ የመከላከልና ህክምና ስራ መሻሻሉን ተናግረዋል።  


በኢትዮጵያ በተሰራዉ ስራ በበሽታዉ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር  ቢቀንስም የቲቢ በሸታ እንዲሁም የቲቢ -ኤች አይቪ ጫና አሁንም ከፍተኛ በሆነባቸዉ 30 አገሮች አንዷ መሆኗን ያወሱት ዶ/ር ሊያ፣ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚሰሩ ስራዎች ለቲቢ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑና የተዘነጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

“በጎነት ለጤናችን’’በሚል ነፃ የጤና ምርመራ እና የህክምና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

voluntary service

በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ሳምንት ከመቶ ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የነጻ የጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግለት ለመስጠት የተጀመረው  ሰው- ተኮር የበጎ ፈቃድ የተግባር ዘመቻ  በሁሉም ክልሎችና በከተማ መስተዳደሮች በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል፡፡


በዘመቻውም የጤና አጠባበቅ ትምህርትና ምክር አገልግሎት ፣ በተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣የኮሌራና ሌሎች ውሀ ወለድ በሽታዎች፣ ወባ፣ ኤች አይ ቪ ፣ ቲቪ ፣ ኮቪድ-19፣ የካንሰር ህመምና ሌሎች ትኩረት በሚሹ የጤና ጉዳዮች ላይ ማለትም የደም ግፊት ፣የደም የስኳር መጠን፣ ከአንገት በላይ፣ የአይን፣ የቆዳ፣የስነ ምግብ፣ የአእምሮ ጤና  እና ሌሎች የጤና አገልግሎቶች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡