Articles

ኦንኮሳርኪያሲስ በሽታን ለማጥፋት የተቋቋመ የኤክስፐርቶች አማካሪ ኮሚቴ 11ኛ አመታዊ ጉባኤውን አካሄደ

Dr.Drje

ኦንኮሳርኪያሲስ የቆዳና የአይን ችግር የሚያስከትል በሽታ ነው። በሽታው ኦንኮሰርካ ቮልቮሉስ በሚባል ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን፤ ምልክቶቹም ከባድ የማሳከክ ስሜት፣ ከቆዳ ስር ያሉ እብጠቶች እና ዓይነ ስውርነት ናቸው። እንደ DEET ያሉ ነፍሳትን የሚከላከሉ መድኃኒቶችን መርጨት እና ረጅም እጅጌ ያላቸውን ሸሚዞች እና ሱሪዎችን በመልበስ በሽታውን መከላከል ይቻላል።

በአመታዊ ጉባኤው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት፤ ኮሚቴው እያደረገ የሚገኘው ኢንቨስትመንት በሽታውን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት እያፋጠነ ይገኛል፡፡ ጤና ሚኒስቴር በሽታው በስፋት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በመጨመር የመከላከል እና አክሞ የማዳን ስራዎችን በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 

የውጪ ሀገር የሕክምና አሰጣጥ ቅብብልሽ ሥርዓት ማስተግበሪያ መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የወጣ ማስታወቂያ

ለሕክምና ወደ ውጪ ሀገር የሚሄድ ኢትዮጵያዊ ጤንነቱ፤ደህንነቱ እና ክብሩ ተጠብቆ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል የሕግ ማእቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ 
በሀገር አቀፍ ደረጃ የውጪ ሀገር የሕክምና ቅብብሎሽን ወጥ የሆነ አተገባበር ስርዓት በመዘርጋት አላስፈላጊ የታካሚን እንግልት መቀነስ፣ ለህክምናው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በተሟላ መልኩ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ 
የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት፣አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 አንቀጽ አንቀፅ 58(2) መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡ 

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም እረቂቅ መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የወጣ ማስታወቂያ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ስልጣን እና በአንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው አስቸኳይ የህክምና እገልግሎት እንዲያገኝ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት  የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም እረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

ረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 05/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡