በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭርሃም ንጉሴ የተመራ ልኡካን ቡድን ከጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ
ኢትዮጵያ እና እስራኤል ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ያስታወሱት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭርሃም ንጉሴ፤ የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጤና ዘርፍ ሁለቱ ሃገራት በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ዋነኛው መሆኑን አምባሳደሩ ያስረዱ ሲሆን፤ በተለይም በልብ ህክምና፣ የጨቅላ እጻናት ጽኑ ህሙማን እና የእናቶች ጤና እንዲሁም የአካል ድጋፍ እና መልሶ ማገገም ዘርፎች ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ ከ1000 ለሚበልጡ ይልብ ህሙማን ህክምና መስጠት የቻለው ሴቭ ቻይልድስ ሃርት ልኡካን ቡድን በጥቁር አንበሳ የልብ ማእከል የልብ ህሙማን ልየታ፣ የባለሙያዎች ስልጠና፣ እና የልብ ቀዶ ህክምና ማድረጉ በውይይቱ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የጽኑ ህሙማን ህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የባለሙያዎች ስልጠና መሰጡትንም ልኡካኑ አስታውቀዋል፡፡