ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የሆስፒታል የአክሪዲቴሽን ስታንዳርድ(ደረጃ) ለህዝብ አስተያየት ክፍት ሆነ፡

  • Time to read less than 1 minute

የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት ጥራት እና ደህንነት ለማረጋገጥ የጤና ተቋማት የአክሪዲቴሽን ስርዓት ማስፈፀሚያ ፍኖተ ካርታ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፤ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ፤ የኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽንና አጋር አካላት እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ አዘጋጅቶ በትግበራ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የጤና ተቋማት በሚሰጡት የጤና አገልግሎት በሃገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች አገልግሎት አክሪዲቴሽን ስታንዳርድ/ደረጃ/ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አዘጋጀቶ ረቂቅ ሰነድ ለህዝብ አስተያየት በይፋ ክፍት ያደረገ ሲሆን እርስዎም ሰነዱን ከዚህ በታች ከተቀመጠዉ ድህረ -ገጽ በማዉረድ አስተያየትዎን በቀረበዉ ቅፅ መሰረት መጠይቁን በአግባቡ በመሙላት አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል፡፡

ለሚሰጡት ገንቢ አስተያየትም በተገልጋይ ማህበረሰባችን ስም ከወዲሁ እናመሰግናለን፡፡

በረቂቅ ሰነዱ ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስተያየቱን ከታች የሚገኘውን ቅፅ በመሙላት በኢሜል አድራሻ (henok.hailu@moh.gov.et) መላክ ወይም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈፃሚ ክፍል በአካል ማስገባት ይቻላል።

የአክሪዲቴሽን ስታንዳርድ(ደረጃ)                  አስተያየት መስጫ ቅፅ

        file download                              file download