የአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ-ኔፓድ የሚኒስትሮች መድረክ  ለተዋልዶ ጤና ትኩረት በመስጠት ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማፋጠን እና የአፍሪካን ስነ-ህዝብ አቅም መጠቀም” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል፡፡ 

Dr Mekdes Daba

በመድረኩ  የተሳተፉ የአፍሪካ ሃገራት ሚኒስትሮች ልምድ የሚለዋወጡበት እና በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን መግባባት ላይ የሚደርሱበት መድረክ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው ያስረዱ ሲሆን፤ ጉባኤው በዋናነት የስነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ትኩረቱን ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ 


ኢትዮጵያ በስነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ማፍሰሷን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፤ በዚህም የእናቶች እና ህጻናት ህልፈትን መቀነስ መቻሉን እና አጠቃላይ የጤና ስርአትንም ማሻሻል መቻሉን አብራርተዋል፡፡ የአፍሪካ ሃገራት የሃገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ አፍሪካ በጤና ዘርፍ እራሷን እንድትችል መስራት ይገባል ያሉት ሚኒስትሯ፤ ያጋጠሙ የፋይናንስ ክፍተቶችን የሃገር ውስጥ ሃብትን በማሳባሰብ እና ከአጋሮች ጋር በትብብር በመስራት መቅረፍ እንደሚገባ አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የሆስፒታል የአክሪዲቴሽን ስታንዳርድ(ደረጃ) ለህዝብ አስተያየት ክፍት ሆነ፡

የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት ጥራት እና ደህንነት ለማረጋገጥ የጤና ተቋማት የአክሪዲቴሽን ስርዓት ማስፈፀሚያ ፍኖተ ካርታ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፤ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ፤ የኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽንና አጋር አካላት እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ አዘጋጅቶ በትግበራ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የጤና ተቋማት በሚሰጡት የጤና አገልግሎት በሃገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች አገልግሎት አክሪዲቴሽን ስታንዳርድ/ደረጃ/ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አዘጋጀቶ ረቂቅ ሰነድ ለህዝብ አስተያየት በይፋ ክፍት ያደረገ ሲሆን እርስዎም ሰነዱን ከዚህ በታች ከተቀመጠዉ ድህረ -ገጽ በማዉረድ አስተያየትዎን በቀረበዉ ቅፅ መሰረት መጠይቁን በአግባቡ በመሙላት አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል፡፡

ለሚሰጡት ገንቢ አስተያየትም በተገልጋይ ማህበረሰባችን ስም ከወዲሁ እናመሰግናለን፡፡

ኦንኮሳርኪያሲስ በሽታን ለማጥፋት የተቋቋመ የኤክስፐርቶች አማካሪ ኮሚቴ 11ኛ አመታዊ ጉባኤውን አካሄደ

ኦንኮሳርኪያሲስ የቆዳና የአይን ችግር የሚያስከትል በሽታ ነው። በሽታው ኦንኮሰርካ ቮልቮሉስ በሚባል ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን፤ ምልክቶቹም ከባድ የማሳከክ ስሜት፣ ከቆዳ ስር ያሉ እብጠቶች እና ዓይነ ስውርነት ናቸው። እንደ DEET ያሉ ነፍሳትን የሚከላከሉ መድኃኒቶችን መርጨት እና ረጅም እጅጌ ያላቸውን ሸሚዞች እና ሱሪዎችን በመልበስ በሽታውን መከላከል ይቻላል።

በአመታዊ ጉባኤው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት፤ ኮሚቴው እያደረገ የሚገኘው ኢንቨስትመንት በሽታውን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት እያፋጠነ ይገኛል፡፡ ጤና ሚኒስቴር በሽታው በስፋት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በመጨመር የመከላከል እና አክሞ የማዳን ስራዎችን በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 

ኦንኮሳርኪያሲስ በሽታን ለማጥፋት የተቋቋመ የኤክስፐርቶች አማካሪ ኮሚቴ 11ኛ አመታዊ ጉባኤውን አካሄደ

Dr.Drje

ኦንኮሳርኪያሲስ የቆዳና የአይን ችግር የሚያስከትል በሽታ ነው። በሽታው ኦንኮሰርካ ቮልቮሉስ በሚባል ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን፤ ምልክቶቹም ከባድ የማሳከክ ስሜት፣ ከቆዳ ስር ያሉ እብጠቶች እና ዓይነ ስውርነት ናቸው። እንደ DEET ያሉ ነፍሳትን የሚከላከሉ መድኃኒቶችን መርጨት እና ረጅም እጅጌ ያላቸውን ሸሚዞች እና ሱሪዎችን በመልበስ በሽታውን መከላከል ይቻላል።

በአመታዊ ጉባኤው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት፤ ኮሚቴው እያደረገ የሚገኘው ኢንቨስትመንት በሽታውን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት እያፋጠነ ይገኛል፡፡ ጤና ሚኒስቴር በሽታው በስፋት በሚገኝባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በመጨመር የመከላከል እና አክሞ የማዳን ስራዎችን በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ 

የውጪ ሀገር የሕክምና አሰጣጥ ቅብብልሽ ሥርዓት ማስተግበሪያ መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የወጣ ማስታወቂያ

ለሕክምና ወደ ውጪ ሀገር የሚሄድ ኢትዮጵያዊ ጤንነቱ፤ደህንነቱ እና ክብሩ ተጠብቆ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል የሕግ ማእቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ 
በሀገር አቀፍ ደረጃ የውጪ ሀገር የሕክምና ቅብብሎሽን ወጥ የሆነ አተገባበር ስርዓት በመዘርጋት አላስፈላጊ የታካሚን እንግልት መቀነስ፣ ለህክምናው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በተሟላ መልኩ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ 
የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት፣አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 አንቀጽ አንቀፅ 58(2) መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡ 

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም እረቂቅ መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የወጣ ማስታወቂያ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ስልጣን እና በአንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው አስቸኳይ የህክምና እገልግሎት እንዲያገኝ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት  የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም እረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

ረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 05/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡

የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች አስቸኳይ ህክምና እና የካሳ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ

የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጅዎች የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ 799/2005 ዓ.ም በጸደቀው መሰረት በሁሉም ጤና ተቋማት እስከ ሁለት ሺህ ብር አገልግሎት በነፃ እንዲያገኙ ተደንግጓል፡፡ ይህንም አዋጅ መሰረት በማድረግ በተሻሻለው በደንብ ቁጥር 554/2016 የድንገተኛ ህክምና ወጪ እስከ አስራ አምስት ሺህ ብር እንዲሻሻል የተደረገ ሲሆን ለዚህም እረቂቅ መመሪያ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ተዘጋጅቷል፡፡

በእረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 05/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡

መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ  ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ ትሰራለች፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ 

Dr. Mekdes Daba

በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገለጸዋል።


በመድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ዙሪያ ለመምከር በተዘጋጀው የከፍተኛ ሃላፊዎች መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ተጽእኖ ለመቀነስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራና ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ አስፋላጊውን ክትትል ማድረግና የምርምር ስራዎችን እንደምታጠናክር ገልጸዋል።  ይህ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስተሯ አስምረውበታል።

ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል እና መቆጣጠር ለስመዘገበችዉ አመርቂ ዉጤት እዉቅና አገኘች

Dr Mekdes Daba

አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማት አበርክቷል።

እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ላስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA77) ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን ተቀብለዋል።