ቀጣይ የሙያ ግንባታ
In order for health workers to provide quality care and meet their communities’ changing health care needs, they must become lifelong learners dedicated to updating their professional knowledge, skil
In order for health workers to provide quality care and meet their communities’ changing health care needs, they must become lifelong learners dedicated to updating their professional knowledge, skil
በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገለጸዋል።
በመድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ዙሪያ ለመምከር በተዘጋጀው የከፍተኛ ሃላፊዎች መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ተጽእኖ ለመቀነስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራና ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ አስፋላጊውን ክትትል ማድረግና የምርምር ስራዎችን እንደምታጠናክር ገልጸዋል። ይህ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስተሯ አስምረውበታል።
አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማት አበርክቷል።
እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ላስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA77) ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን ተቀብለዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ያስታወሱት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭርሃም ንጉሴ፤ የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጤና ዘርፍ ሁለቱ ሃገራት በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ዋነኛው መሆኑን አምባሳደሩ ያስረዱ ሲሆን፤ በተለይም በልብ ህክምና፣ የጨቅላ እጻናት ጽኑ ህሙማን እና የእናቶች ጤና እንዲሁም የአካል ድጋፍ እና መልሶ ማገገም ዘርፎች ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ ከ1000 ለሚበልጡ ይልብ ህሙማን ህክምና መስጠት የቻለው ሴቭ ቻይልድስ ሃርት ልኡካን ቡድን በጥቁር አንበሳ የልብ ማእከል የልብ ህሙማን ልየታ፣ የባለሙያዎች ስልጠና፣ እና የልብ ቀዶ ህክምና ማድረጉ በውይይቱ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የጽኑ ህሙማን ህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የባለሙያዎች ስልጠና መሰጡትንም ልኡካኑ አስታውቀዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር ዉይይት ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ተደረሽ ለማድረግ፣ ጤናን እና ስነ ምግብን፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እና የኤስዲጂ ኢላማዎች ከግብ እንዲደርሱ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር ጠንካራ አጋርነት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር በተደረገው ውይይት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ሚኒስትሯ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
እ.ኤ.አ. ከ 2018 በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል ጌትስ ከጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋርም ዉይይት አድርገዋል።
በብራዛቪል ኮንጎ እየተካሄደ ያለዉ 74ኛው የአፍሪካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ቀጥሏል።
በመድረኩ በአፍሪካ በተለያዩ ግዜያት ወረርሽኞችና ሌሎች ድንገተኛ የጤና አደጋዎች እየተከሰቱ የማህበረሰቡ ጤና ስጋት መሆናቸዉ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል።
ኢቦላ፣ ኮቪድ 19 እና ሌሎች ወረርሽኞች በአፍርካ ቀጠና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በማስታወስ አሁን ላይ ኤም ፖክስ (Mpox) የደቀነዉ የጤና አደጋ በተለይ ለአፍሪካ አሳሳቢ መሆኑ ተንስተዋል።
በመደረኩ ላይ በመገኘት ሀሳባቸዉን ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ (Mpox) የተጠረጠረም ሆነ የተያዘ ሰዉ አለመኖሩን ጠቅሰዉ በሽታዉ እንዳይከሰት፣ ከተከሰተም ለመቆጣጠር የሚያስችል ሰፊ የቅደመ መከላከልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል።
በታንዛኒያ አቅራቢነት የተወዳደሩት ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ አባል አገራት በሰጡት ድምጽ አብላጫ በማግኘት ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል።
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት እንዲመሩ በመሰየማቸዉ እንኳን ደስ ያሎት ብለዋቸዋል።
ጤና ሚኒስቴር በጤና ተቋማት የሚሰጡ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል የማህበረሰብ አስተያየት መመዘኛ ካርድ (community Score Card) እየተገበረ ሲሆን በዚህ የአተገባበር ስርዓት ዙርያ ኢትዮጵያ ያላትን አሰራርና ልምድ ለማካፈል ብሎም በጋና ሀገር ያለውን የማህበረሰብ አስተያየት መመዘኛ ስርዓት ትግበራ ተሞክሮ ለመቅሰም ከተለያዩ የስራ ክፍሎችና ክልሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ቡድን በጋና ሀገር ልምድ ልዉዉጥ እያደረገ ይገኛል።
በጉብኝቱ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ጤና ጣቢያ የምግብና የስርአተ ምግብ ስትራቴጂን አተገባበር የተጎበኘ ሲሆን የሰቆጣ ቃልክዳን በስምምነቱ መሰረት በመተግበር በርካታ እፃናት ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም ተገልጿል።
በሌማት ቱሩፋት እና የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በተወሰዱ እርምጃዎችም የቢዮ አዋሌ ነዋሪዎች ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገብ መቻሉ ተነስቷል።
ከጉብኝቱ በተጨማሪም የችግኝ ተከላ መርሃግብርም ተከናውኗል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጄኤስአይ ዋና ስራ አስፈጻሚና ፕሬዝደንት ማርጋሪት ክሮቲ እና የጂኤስአይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ተደርገው አዲስ የተሾሙት ዶ/ር ቢኒያም ደስታ ጋር ተወያዩ ።
የጄኤስአይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር መሰየሙ በጤና ሚኒስቴር እና ጄኤስአይ መሃል ያለውን ትብብር እና ግንኙነት እንደሚያጠናክር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በውይይታቸው የገለጹ ሲሆን፤ ጄኤስአይ የጤና ሚኒስቴር ጠንካራ አጋር መሆኑን እና ጤና ሚኒስቴር አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡