eCHIS

echis

eCHIS

የኤሌክትሮኒክ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና የመረጃ ስርዓት (eCHIS) በመረጃ አብዮት ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው ዋና
ተግባራት መካከል አንዱ ነው። የኢትዮጲያ የጤና አክስቴንሽን ፕሮግራም ስኬታማ ሆኖ በማህበረሰብ ደረጃ ለውጥ ማምጣት
የቻለ እሳቤ ሲሆን፣ የዚህ እሳቤ አንዱ አካል በወረቀት ላይ የተመሰረትው የመረጃ ስርዓቱ ነው። eCHIS ይህን ከ1997
ዓ.ም ጀምሮ ሲሰራበት የነበረውን የወረቀት የመረጃ ስርዓት (CHIS) ወደ ኤሌክትሮኒክ ለመቀየር ታልሞ የተፈጠረ ነው።
በዚህም ዘመናዊ የመረጃ ስርዓትን ለጤና አክስቴንሽን ሰራተኞች በማቅረብ የሚከተሉትን ለማሳካት ተችሏል:-

  • የጤና ኤክስቴናሽን ሰራተኞችን ስራ የሚያቃልል የስራ ላይ አጋዥ መረጃ ማቅረብ
  • በጤና ኬላ እና ጤና ጣቢያ መካከል የተቀላጠፈ የመረጃ ልውውጥ እና የህሙማን ቅብብሎሽ
  • ለክትትል የሚያመች የህሙማን እና ደንበኞች መረጃ አያያዝ
  • የተሰጡ አገልግሎቶችን በቀላሉ ሪፖርት ማድረግ እና መረጃውን ከማዕከል መተንተን

eCHIS የሞባይል መተግበሪያ እና የመከታተያ ድረገጽ ያለው ሲሆን eCHISን ማልማት የተጀመረው የቤተሰብ ማህደርን ወደ ሞባይል መተግበሪያ በመቀየር ነው። እያንዳንዱ ቤተሰብ እና የቤተሰብ አባላት በeCHIS የሚመዘገቡ ሲሆን፤ በቤተሰብ ደረጃ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ተግበራን፣ ሞዴል አባወራን፣ የሴቶች የልማት ቡድንን፣ እና የቤት አያያዘና ያአኗኗር ሁኔታን ለመከተተል ያስችላል። በግለሰብ ደረጃ የተለያዩ በጤና ኤክስቴንሽኝ ደረጃ የመሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን (services) ለመከታተል ያስችላል። እነዚህ አገልግሎቶች (services) ደረጃ በደረጃ በተለያዩ ሞጁሎች በልጽገው ወደ ትግበራ እየገቡ ይገኛሉ።


የቤተሰብ ማህደር እና የእናቶች እና የጨቅላ ህጻናት ሞጁሎች በልጽገው እና የሙከራ ትግበራን አልፈው በስምንት ክሎሎች፣ ማለትም በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ ሃረሪ፣ ድሬዳዋ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በ3,180 ጤና ኬላዎች ተተግብረው የጤና ኤክስቴናሽን ሰራተኞች እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ። የስነ-ምግብ እና የህጻናት ህክምና ሞጁሎች በልጽገው የሙከራ ትግበራ ላይ ናቸው። እንዲሁም ከበሽታ መከላከል የቲቢ እና የወባ ሞጁሎች በልጽገው የሙከራ ትግበራ ላይ ይገኛሉ። የኮቪድ-19ን የማህበረሰብ አቅፍ ተጋላጭነት ዳሰሳ ለማድረግ የሚያስችል ሞጁል በለጽጎ ወደ ስራ ገብቷል። የNTD (Neglected tropical diseases)፣ NCD (ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች) እና HIV ሞጁሎች የማበልፀግ ስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን በያዝነው በጀት አመት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል።


eCHIS ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ በተለያዩ አገርኛ ቋንቋዎች (አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ) ተተርጉሟል። ትግበራውን ለማሳለጥ በየደረጃው ለክልል ዞን እና ወረዳ ባለሙያውች ስልጠና ተሰጥቷል። ከኢትዮቴሌኮም ጋር በመተባበር የተለዩ (Machine to Machine) ሲምካርዶች ለትግበራው ተዘጋጅተው ተሰራጭተዋል። እንዲሁም ከስታቲስቲክስ ባለስልጣን የተገኙ የሚጠበቀውን ድረጃ ባያሙሉም ለጊዜው የሚያገለግሉ 32,000 ታብሌት ክምፒዩተሮች ተሰራጭተዋል። በቀጣይ eCHISን በአርሶ አደር ክልል ጤና ኬላዎች ወስጥ ለሁሉም ለማዳረስ እና የከተማ እና የአርብቶ አደር ሲሪቶችን (editions) አበልጽጎ ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።

workflow
eCHIS Workflow