ኢትዮጵያ ጤናማና አምራች የሆነች አፍርካ እንዲኖረን ከአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር  በትብብር መስራቷንና እያደረገች ያለዉን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች-የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

  • Time to read less than 1 minute
Dr Mekdes Daba

ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል። 


በታንዛኒያ አቅራቢነት የተወዳደሩት ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ አባል አገራት በሰጡት ድምጽ አብላጫ በማግኘት ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል። 


የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት እንዲመሩ በመሰየማቸዉ እንኳን ደስ ያሎት ብለዋቸዋል።  


ኢትዮጵያ ጤናማና አምራች የሆነች አፍርካ እንዲኖረን ከአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በትብብር እንደምትሰራና እያደረገች ያለዉን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዉላቸዋል።