የእናቶች ጤና
በኢትዮጵያ የእናቶች ጤና አጠቃላይ እይታ
ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በእናቶች ሞት ላይ አስገራሚ ለውጥ አድርጋለች፣ MMR በ 2000ዓ.ም 871 ከ100,000 የነበረ ሲሆን በ2017ዓ.ም ወደ 401 ከ100,000 ቀንሷል፤ ይህ በየዓመቱ ወደ 12,000 የእናቶች ሞት ነው። ቀጥተኛ የወሊድ ችግሮች 85% የሚሆኑት የሞት መንስኤዎች ናቸው። የረጅም ጊዜ ሁኔታዎች ሴቶች ላይ ከወሊድ ጋር የተዛመዱ በሽታዎችን አስከትለዋል። ለምሳሌ ፊስቱላ ፣ የማሕፀን ተፈጥሯዊ ቦታ መዛባት፣ ሥር የሰደደ የወገብ አጥንት ህመም ፣ ድብርት እና ድካም። በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ፊስቱላ የተለመደ ሲሆን በዋነኝነት በልጃገርረድ ዕድሜ ከሚፈጠር እርግዝና እና ችላ ከተባለ ረዥም ምጥ ጋር ተዳምሮ የሚፈጥረው ነው። ከፍተኛ የእናቶች ሞት መጠን በቀጥታ ከ ከፍተኛ የአራስ ሕፃናትሞት መጠን (29/1,000 በህይወት የተወለዱ ህጻናት )ጋር ይያያዛል። ይህ በወሊድ ጊዜ እናቶቹ የነበሩበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያንፀባርቃል። ለአራስ ሕፃናት ሞት ዋነኛ መንስኤ
- Read more about የእናቶች ጤና
- 2291 views