Wafid Fast-Track Accreditation for Ethiopian Hospital and Medical Centers

የጤና ሚኒስቴር የዋፊድ ፕሮግራም የምዝገባ ሂደት የተሳለጠ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ በማቀድ፣ የመንግስት እና የግል ጤና ተቋማት ይህንን ፕሮግራም ለመቀላቀል የሚያስችላቸው የምዝገባ መድረክ በማዘጋጀት በጤና ሚኒስቴር ድኅረ ገጽ ላይ የመመዝገቢያ ማስፈንጠሪያ አያይዘን ማውጣታችን ይታወሳል።

በዚህም መሠረት በዚህ ፕሮግራም ላይ የተመዘገባችሁ እና የተቋሙን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልታችሁ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ ነባር እና አዲስ የመንግስት እንዲሁም የግል የጤና ተቋማት የዋፊድ ፕሮግራም አካላዊ ግምገማ (evaluation) መርሀ ግብር ከ ጥር 19 ,2017 - ጥር 27, 2017 መሆኑን ተቋሙ የገለጸ በመሆኑ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠባበቁ ለማሳወቅ እንወዳለን።