HPCAL Announcements

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

_____________

ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Nursing, Nutrition, Optometry, Pediatric and Child Health Nursing, Dental Medicine, Emergency and Critical Care Nursing, Environmental Health, Surgical Nursing, Anesthesia, Psychiatric Nursing, Pharmacy, Medical Radiology Technology, Midwifery, Medicine, Public Health and Medical Laboratory Science ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከሚያዚያ 1 - 3/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦

1. የፈተናው መርሃ-ግብር

  • በ01/08/2017 ዓ.ም…… Nursing, Nutrition, Optometry, Pediatric and Child Health Nursing, Dental Medicine, Emergency and Critical Care Nursing, Environmental Health, Surgical Nursing, Anesthesia and Psychiatric Nursing
  • በ02/08/2017 ዓ.ም…… Pharmacy, Medical Radiology Technology, Midwifery
  • በ03/08/2017 ዓ.ም…… Medicine, Public Health and Medical Laboratory Science

ሁሉም ተፈታኝ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::

2. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

3. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎችን፣ እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

4. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣

5. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እያሳሰብን:-

  • ተመዛኞች ወደ ጣቢያ ከመምጣታችሁ በፊት ከዚህ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘውን attachment በመክፈት የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያዎች መመልከት ይኖርባችኋል።
  • ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
  • በፈተና ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በስልክ ቁጥር 0115186275/ 0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች

ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመጫን የጤና ባለሙያዎች ብቃት ምዘና ፈተና መስጫ  የኦንላይን መተግበሪያ አጠቃቀምን በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ።

coc

https://www.youtube.com/watch?v=H2JGL7d-4F8

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/M0H_EThiopia/494?single