ዶ/ር አስናቀ ዋቅጅራ ደሬሳ

Dr. Asnake Waqjira Deresa
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ሚንስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ

ዶ/ር አስናቀ ዋቅጅራ ደሬሳ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ሚንስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ናቸው።  በዚህ የስራ አመራር ዘርፍ ስር ስምንት ስራ አስፈፃሚዎች አሉ። ይህ የስራ ዘርፍ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የዕለት ተዕለት የአመራር እና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችን ይከታተላል፣ ይደግፋል እንዲሁም አመራር ይሰጣል፡፡
ዶ/ር አስናቀ ዋቅጅራ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና መንግስታዊ ባልሆኑ አጋር ድርጅቶች በአመራር እና በከፍተኛ አማካሪነት ሰፊ ልምድ ያላቸው ሲሆን ለምሳሌ ያህል በቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና የስራ አመራር ቦርድ ፀሀፊ፣ የጠቅላላ እና የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ሱፐርቫይዘር፣ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ እና የኦሮምያ ክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ አማካሪ፣ በኮሉምቢያ ዩኒቨርሲቲ አይካፕ ኢትዮጵያ፣ በሰርት ኢትዮጵያ፣ አማካሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ ባገኙት በርካታ ስልጠናዎችም በመታገዝ የተለያዩ ጥናቶችን፣ የአሰራር ስልቶችን፣ መመሪያዎችን እና የስልጠና ማቴርያሎችን በማዘጋጀት ሰፊ ስራ ሰርተዋል። በዚህም በአመራር ዘመናቸው የኢትዮጵያን 1ኛ ደረጃ የላቀ ጥራት ተሸላሚ ከመሆን ጀምሮ ብዙ ክልላዊ፣ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ እውቅናዎችን እና ሽልማቶችን አግኝተዋል፡፡