የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የወጣ ማስታወቂያ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ስልጣን እና በአንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው አስቸኳይ የህክምና እገልግሎት እንዲያገኝ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት  የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም እረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

 

ማንኛውም እረቂቅ የመመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚፈልግ ሰው ቀጥሎ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም በነፃ ማውረድ ይችላል፡፡

                                                          Image removed.

በእረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 5/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በሞምላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡

One file only.
2 ኤምቢ limit.
Allowed types: gif jpg png bmp eps tif pict psd txt rtf html odf pdf doc docx ppt pptx xls xlsx xml avi mov mp3 ogg wav bz2 dmg gz jar rar sit svg tar zip.