በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጥፋት ቡድኑ ባደረሰው ጉዳት ተፈናቅለው ባህርዳር ለሚገኙ ወገኖችና በክልሉ ውስጥ ጉዳት ለደረሰባቸው 15 ጤና ጣቢያዎች ድጋፍ ተደረገ
በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴአታ ወ/ሮ ሠሐረላ አብዱላሂ የተመራ ከጤና ሚኒስቴር፤ ፌዴራል ሆስፒታሎችና ከተጠሪ ተቋማትና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጣ ቡድን በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ በህውሃት የጥፋት ቡድን ባደረሰባቸው ጉዳት ተፈናቅለው ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን ጎብኝቷል።
ቡድኑ ከደሴና ኮምቦልቻ አከባቢ በፀጥታው ችግር ምክንያት ተፋናቅለው በባህርዳር ከተማ በዘንዘልማ የተፈናቃዮች መጠለያ የሚገኙትን የጎበኙ ሲሆን በከተማው አስራ አራት ሺ አምስት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች እንደሚገኙና በመጠለያ ቦታው አራት ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት ተፈናቃዮች የሚገኙ መሆኑ ታውቋል፡፡ ለተፈናቀሉ ወገኖች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የክልሉ ጤና ቢሮ ባለሙያዎችን መድቦ ክሊኒክ የከፈተላቸው ሲሆን ከተፈናቀሉ የጤና ባለሙያዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የህክምና አገልግሎትና የማልኑትሪሽን ችግር ልየታ ስራ እየተሰራ መሆኑን መመልከት ተችለዋል።