- 2 views
ወ/ሮ ህይወት ዳርሰኔ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሃዋሳ ዩንቨርስቲ በህብረተሰብ ጤና እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከጎንደር ዮንቨርስቲ በአፕላይድ ሁማን ኑትሪሸን( Applied Human Nutrition) አግኝተዋል፡፡
ወ/ሮ ህይወት ዳርሰኔ በጤና ተቛማት አስተዳደር፥ በህፃናትና አዋቂዎች ህክምና ፣በኤች አይቪ ኤድስ ህክምናና ምክር አገልግሎት ፥ በስርዓተ ፆታ፥በመከላከል-ተኮር ሥርዓተ-ምግብ አገልግሎት፥በአጣዳፊ መካከለኛ እና ከፍተኛ የምግብ አለመመጣጠን የምገባ-ህክምና አገልግሎት ፥በምግብና ስርዓተ ምግብ ዘርፈ-ብዙ ቅንጅታዊ አሰራር ዘርፈ ብዙ ተሞክሮዎችና አገልግሎት አላቸው፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ ክልል የክልሉ የስርዓተ ፆታ አስተባባሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የክልሉ የጥናትና ምርምር የቦርድ አባል በመሆንም በጤና ተቛማት የሚማሩ ተመራቂ ተማሪዎችን የማማከር አገልግሎት በመስጠት አገልግለዋል፡፡
ወ/ሮ ህይወት በጤና ሚኒስትቴር የስርዓተ ምግብ ክፍሉን የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ኦፊሰር በመሆን የተቀላለቀሉ ሲሆን የብሄራዊ ምግብና ስርዓተ ምግብ ቴክኒካል ኮሚቴ አባል በመሆንም የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጅና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች ዝግጅትና ትግበራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ መሪዎች ኔትዎርክ አባልና የስርዓተ ምግብ መሪዎች ስልጠናም 2ተኛው አልሙኒ ናቸው፡፡
ወ/ሮ ህይወት የብሄራዊ ምግብና ስርዓተ ምግብ ቴክኒካል ኮሚቴ እና አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢና ፀሃፊ በመሆንም አገልግለዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ወ/ሮ ህይወት ዳርሰኔ በጤና ሚኒስቴር ሥርዓተ-ምግብ ማስተባባሪያ ጽ/ቤት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኦፊሰር እና የብሄራዊ ምግብና ስርዓተ ምግብ ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡