የማህበረሰብ ተሳትፎና እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ መሪ ሥራ አስፈፃሚ

ራዕይ፡

  • ጤናማ፣ አምራች እና የበለጸገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት

ተልዕኮ፡

  • የተቀናጀ፣ በሳይንስ የተረጋገጡ እና በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያላቸውን ቴክኖሎጂዎችንና ዜዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን፣ የቤተሰቦችን እንዲሁም የማህበረሰብ ጤናን ማሻሻል ነው፡፡

የሥራ አስፈጻማው ተግባርና ሃላፊነት

ሥራ አስፈጻማው በዋናነት ሶስት አንኳር ተግባራትን ማለትም የማህበረሰብ የጤና ባለቤትንትን ማሻሻል፣ በጤና ጣቢዎችና በጤና ኬላዎች የሚሰጠውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትንና ጥራትን ማሻሻል እንዲሁም የአከባቢ ጤና አገልግሎቶችን አጠናክሮ በመተግበር ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ለማሳካት የሚደረገውን ጉዞ ማፋጠን ሲሆን ከዚህ የሚከተሉትን ተግባራትን አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይደግፋል ያስተባብራል፡፡

  • የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ተግባራትን አፈጻጸም ይከታተላል፤ ይደግፋል
  • የማህበረሰብ ተሳትፎና ባለቤትነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችን ይቀይሳል፤ ይተገብራል፤
  • የወረዳ ትራንስፎርሜሽን ተግባራት አፈጻጸምን ይከታተላል፣ ይደግፋል
  • የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ስትራቴጂክ ማዕቀፍ ትግበራን ይከታተላል፤ ይደግፋል
  • የትምህርት ቤት ጤና አገልግሎትን በማሻሻልና ትምህርት ቤቶችን በጤና ሞዴል የማድረግ ስራዎችን ይቀይሳል፣ ትግበራውንም ያስተባብራል፤
  • በጤና ጣቢያዎች የሚሰጡትን የጤና አገልግሎት ተግባራትን ጥራት፣ ተደራሽነታቸውንና ዘላቂነታቸውን ይከታተላል፤
  • የኢትዮጽያ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ጥምረት ለጥራት ሪፎርም ትግበራን ይከታተላል ይደግፋል
  • የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት የህክምና መስጫ መመሪያን አተገባበር ይከታተላል፣ያጠናክራል፣ ተጨማሪ አጋዥ ሰነዶችን ያዘጋጃል
  • ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የጤና ተቋማት ለስራ ሚቹና ከብክሌት የጸዱ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
  • በጤና ተቋማት ክሊኒካል ተግባቦት ክህሎት አንዲዳብር የሚሰሩ ስራዎችን ይከታተላል ያስተባብራል፤ 
  • በከተሞች የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ሪፎርም ትግበራን ይከታተላል፤
  • ተያያዥነት ያላቸውን ስትራቴጂዎች፣መመሪያዎችን እና የአሰራር ስርዓቶችን የማዘጋጀት ተግባራትን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
  • ተቋማዊ አደረጃጀቶችን አሰራሮችን በመዘርጋትና በማጠናከር የተግባራ አፈጻጸምን ማሻሻል
  • የሃብት አሰባሰብን በማጠናከርና አጠቃቀሙንም በማሻሻል የፕሮግራም አፈጻጸምን ማሻሻል
  • የተለያዩ የአቅም ግንባታ ተግባራትን ለፈጻሚዎችና ለባለድርሻ አካላት ማመቻቸትና መስጠት
  • የግል ጤና ተቋማትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድረሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ማሻሻልና ማጠናከር
  • መረጃዎችን በአግባቡ በመሰብሰብና በመተንተን የፕሮግራም አፈጻጸምን መከታተል እንዲሁም የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድና በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን ማዳበር
  • ጥሩ ተሞክሮዎችን በመለየት፣ በመቀመርና በመሰነድ ወደ ሌሎች አከባቢዎች የሚሰፉበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት