በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ አትዮጵያውያ የተሰባሰቡ መድኃኒቶች ጥቃት ለተፈጸመባቸው የህክምና ተቋማት ማሰራጨት ተጀመረ።
የጤና ሚኒስቴር ከዲያስፖራው ማህበረሰብ የተደረጉ ድጋፎችን በተቀናጀ መልኩ እንዲሰበሰብ፣ እንዲለይና በጦርነቱ ለተጎዱ ጤና ተቋማት ከተደለደለ በኋላ ስርጭቱ እንዲከናወን በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለየጤና ተቋማቱ ከየካቲት 04/2014 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭት እያከናወነ ሲሆን እስካሁንም ሸዋሮቢት፣ በአጣዮ ሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ፣ በከሚሴ ሆስፒታል፣ በኮንቦልቻ ሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ፣ በደሴ ሆስፒታል፣ በሰኞ ገበያ ጤና ጣቢያ፣ እና በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ድጋፉን ማድረስ ተችሏል። በመቀጠልም አፋር ክልልን ጨምሮ በተቀሩ አከባቢዎች የሚሰራጭ ይሆናል።