የጤና ሚኒስቴር ከቻይና መንግስት 10 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ተረከበ።
የቻይና መንግስት ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ቃል ገብቶት ከነበረው የ20 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ውስጥ 10 ሚሊዮኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ዛኦ ዚያን እጅ በዛሬው እለት ተረክበዋል፡፡
በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የቻይና መንግስት የኮቪድ 19 በሽታን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እያደረገው ስላለው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል። ለኢትዮጵያ ድጋፍ ከተደረገው 10 ሚሊዮን ውስጥ 5 ሚሊየን የሚሆነው በቻይና መንግስት ቀዳማዊት እመቤት የተበረከተ ሲሆን በአቻቸው የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ስም ለጤና ሚኒስቴር የደረሰ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ሊያ ክትባቱም በዋነኝነት ተደራሽ የሚያደርገው ለእናቶች እና ለወጣቶች መሆኑንም አክለው ተናግረዋል፡፡
- Read more about የጤና ሚኒስቴር ከቻይና መንግስት 10 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ተረከበ።
- Log in or register to post comments