የማንኛውም ተቋም የመንግስትም ይሁን የግል ስኬት በስሙ ላይ በእጅጉ የተመካ ነው። የተገልጋዮች፣ የሰራተኞች ፣ የባለሀብቶች ፣ የፖሊሲ አውጪዎች እና የመገናኛ ብዙኃን አስተያየቶች በአንድ ድርጅት ብልጽግና ላይ ኃይለኛ ተፅእኖ አላቸው። ስለ ተቋሙ ያላቸው ግንዛቤ ከተቋሙ ጋር መሥራትና መደገፍ ይፈልጉ እንደሆነ ውሳኔዎቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት የድርጅትን ስም ለመገንባት፣ ግንዛቤን እና ድጋፍን ለማግኘት እንዲሁም በሕዝብ አስተያየትና ባህሪ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ጠንካራ የግንኙነት መስመር አስፈላጊነት የማይካድ ነው።
የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም (FMOH) እንደ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መሠረታዊ የመረጃ መርህ ይመራል። የጊዜው ግሎባላይዜሽን ከመቼውም ጊዜ በላይ የተስፋፋ ሲሆን የደንበኞችን ተለዋዋጭነትና የተሻሉ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ፍላጎትን አሳድጓል። በተመሳሳይ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፣ የመድኃኒቶች ፣ አዳዲስ የፈጠራ በሽታ መከላከያ ስትራቴጂዎችና ግሩም የምርምር ግኝቶች መመስረት ከፍተኛ ተወዳዳሪ ገበያ ፈጥሯል። ስለሆነም መንግስት የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ቀልጣፋና ሁሉን አቀፍ የግንኙነት ስትራቴጂን ለመጠቀም የሚያስችለውን የጤና አገልግሎት ማሻሻያ አስፈላጊነት ተገንዝቧል።
ስለሆነም የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት (PRCD) በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በባለድርሻ አካላት መካከል መልካም ፈቃድንና የጋራ መግባባትን ለመፍጠር እና ለመጠበቅ የተቋቋመ ሲሆን የዳይሬክቶሬቱ ራዕይ የጤና ፖሊሲዎች ፣ ስትራቴጂዎችና አፈፃፀማቸው ላይ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በአግባቡ የሚጠቀም ጤናማና የበለፀገ ማህበረሰብን መፍጠር ነው:: ከዚህም በላይ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃን ማግኘት ህብረተሰቡ የጋራ መግባባት ኖሮት በኢትዮጵያ እድገት ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ያስችለዋል ተብሎ ይታመናል።
ስትራቴጂያዊ ዓላማዎች
BPR ከ PRHCD ጋር በተያያዘ ዓላማው ውጤታማ እና ቀልጣፋ የመረጃ ግንኙነት አውታረ መረብ ማቋቋም ነው:
ህብረተሰብ፣ ባለድርሻ አካላትና የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች ጤናማ፣ አምራችና የበለፀገ ማህበረሰብ የመፍጠር ግባቸውን ለማሳካት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃን ማቅረብ።
የሚኒስቴሩን አቅም ለማጠናከር፣ ለሕጋዊ የሕዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና ከሁሉም በላይ የህዝብ ባህሪ ለውጥ ለማምጣት በጤና ሚኒስትር፣ በክልል ጤና ቢሮዎች (RHBS) እና በሌሎች ወኪል ቢሮዎች መካከል ውጤታማ የመረጃ መረብ መዘርጋት።
የጉዳይ ቡድኖች
የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አምስት የጉዳይ ቡድኖች አሉት፡
- አዲስ ሚዲያና ዌብ ፖርታል ጉዳይ ቡድን
- የሁነት እና ሚዲያ ግንኙነት ጉዳይ ቡድን
- የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ጉዳይ ቡድን
- የህትመት ሚዲያ ፕሮዳክሽን ጉዳይ ቡድን
- የምክር እና ጤና መረጃ ጉዳይ ቡድን
ዋና ሚናዎች እና ኃላፊነቶች
- በሚኒስቴሩ እንዲሁም በክልል ጤና ቢሮዎች ውስጥ በተለያዩ ዋና እና ደጋፊ ሂደቶች መካከል የመረጃ መረብን ማቋቋም እና ዘላቂነትን ማረጋገጥ
- የህትመት ቁሳቁሶች፣ የመረጃ ዴስክ፣ የሀብት ማእከል፣ የመገናኛ ብዙኃንና ድህረ ገፆችን ጨምሮ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫዎች በመጠቀም ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን በማሰራጨት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ/የመረጃ የትኩረት ነጥብ ሆኖ መስራት
- ለሚኒስቴሩ ጥሩ ገጽታ ለመፍጠርና የህዝብ ድጋፍን ለማግኘት የታቀዱ የተለያዩ የህዝብ ግንኙነት ዝግጅቶችን ማቀድ፣ ማስተባበርና መስፈፀም
- ቁልፍ መልዕክቶች፣ ዋና ዋና ዝግጅቶችና የጤና ሴክተር ስኬቶች በቂ የሚዲያ ሽፋን ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ ከሚዲያ ድርጅቶች (ቲቪ እና ሬዲዮን ጨምሮ) ጋር መገናኘት
- በሚኒስቴሩ እና በተለያዩ የሚዲያ ድርጅቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የፕሬስ መግለጫዎችን/የፕሬስ ኮንፈረንሶችን ማስተባበር
- ለሚዲያ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠትና ሁሉም ምላሾች በ PRHCD ወይም በሚኒስቴሩ ውስጥ በሚመለከታቸው ሌሎች አካላት መሰጠታቸውን ማረጋገጥ
- ከሚመለከታቸው አካላት ትክክለኛ ፈቃድ ለሚያቀርቡ የውጭ ጋዜጠኞችና የፊልም ባለሙያዎች መረጃ እና ድጋፍ መስጠት
- የአለምአቀፍና የሀገር ውስጥ የሚዲያ ሪፖርቶችን በመከታተል ፣ ሁኔታዊ ትንተናዎችን በማካሄድና የህዝብና የባለሙያ አስተያየቶችን በመመርመር ለተገቢ እርምጃ የሚረዱ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት
- የመረጃ ግልፅነትን ለማስጠበቅ እና በሚኒስቴሩ ፖሊሲዎች ፣ መመሪያዎች እና ደንቦች ላይ ብሔራዊ መግባባትን ለማሳደግ የፓናል ውይይቶችንና መድረኮችን ማደራጀት
- ከጤና ሚኒስትርና ከሌሎች የመንግስት አካላት የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስላሥልጣናት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የልማት አጋሮች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና የሲቪል ማህበረሰብ የሚሳተፉበት የመስክ ጉዞዎችንና የጤና ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ሳይት ጉብኝቶችን በማደራጀት የተለያዩ ስኬቶችን ማስተዋወቅ።
- የFMoH አርማዎችን ዲዛይን ማድረግ ፣ ኦዲዮ-ቪዥዋል ቁሳቁሶችን እንዲሁም የተለያዩ የህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ ህትመቶችን ለውስጥም ሆነ ለውጭ ፍጆታ ማምረት
- ሁሉም የማስተዋወቂያ ሥራዎች ለህብረተሰቡ ግልጽ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉና ከሚኒስቴሩ ህጎች እና መመሪያዎች ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ
- የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትን ሁሉንም እንቅስቃሴዎች በየጊዜው መከታተልና መገምገም እንዲሁም አፈፃፀምን የሚያሻሽሉ አዳዲስ ዘዴዎችን መምረጥ
የአስተዳደር ሚና
- የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በተቋማዊ መመሪያዎች መሠረት መደራጀቱን ማረጋገጥ እና አስፈላጊውን በጀት ፣ የሰው ኃይልና መሳሪያዎች መገኘት ማረጋገጥ
- በብሔራዊ መመሪያዎች እንዲሁም በሚኒስቴሩ ስትራቴጂክና ዓመታዊ ዕቅዶች ላይ የተመሠረተ የግንኙነት ስትራቴጂ መንደፍ
- የተነደፈው የግንኙነት ስትራቴጂ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን፣ በቂ ድጋፍ መሰጠቱን እና ስኬታማ ውጤት መገኘቱን ለማረጋገጥ የግምገማ እና የክትትል ዘዴን ማቋቋም
- በግንኙነት ስትራቴጂው ሂደት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሪፖርቶችን እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማግኘታቸውን ማረጋገጥ
- ብቁ እና በስነምግባር የታነጹ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን ለማየት የተለያዩ ስልጠናዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ማቀድና ማስፈፀም
- የህዝብ ግንኙነትና አጠቃላይ የጤና አገልግሎቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የህዝብ ሃሳቦችን ፣ አስተያየቶችን እና ጥቆማዎችን እንደ ግብዓት መጠቀም