ከ21 የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የጤና እና የፋይናንስ አመራርና ባለሙያዎች የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

  • Time to read less than 1 minute
news

በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና በሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ አስጎብኝነት በአድዋ ድል መታሰቢያ ተገኝተው የጎበኙት ከ21 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ የጤና እና የፋይናስ አመራርና ባለሙያዎች የጥቁር ህዝቦችን እውነተኛ ተጋድሎና የድል ብስራት ምን ይመስል እንደነበር የሚያመላክት የቅርስ ስብስቦች በአደዋ ድል መታሰቢያ ሙዝዚየም ተደራጅተው መቅረባቸው የኢትዮጵያን የእድገት ጉዞ በደምብ አሳይቶናል ብለዋል።

ለስብሰባ በኢትዮጵያ የተገኙት የUNFPA እና የአለም ጤና ድርጅት ጎብኚዎች የሰው ዘር መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ተገኝተው ይሄንን የመሰለ ታሪካዊ ቦታ በመጎብኘታቸው ደስታቸውን በአድናቆት ገልፀዋል።

የአደዋ ድል መታሰቢያን ከጎበኙ በኃላ በሰጡት አስተያየት በአዲስ አበባ ከተማ እየመጣ ባለዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ መደመማቸዉን ገልጸው ኢትዮጵያ ነጻነቷን አስከብራ ለጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት እንደሆነች ሁሉ በልማቱም የአፍሪካ ምሳሌ መሆኗ የማይቀር መሆኑን ገልጸዋል።

አፍሪካውያን የኩራት ምንጭ የሆኑ ታሪካዊ ስኬቶችን የሚዘክር የስራ ውጤት ማየት በመቻላቸዉ መደሰታቸዉን ተናግረዋል።

ክብርት ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ከጎብኚዎቹ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።