ፕሮጀክቶች የተከናወኑት አገራችን በተለያዩ ችግሮች ማለትም ኮቪድ 19፣ የተለያዩ ግጭቶች እና ድርቅ ውስጥ በነበርችበት ጊዜ ቢሆንም፣ ፈንዱን በመጠቀም አበረታች ውጤቶችን ለማስመዝገብ ተችላል። የተገኙ ውጤቶችን ለማስፋፋትና ያጋጠሙ ችግሮችን በዘላቅነት ለመፍታት የሚያስችል አውደ ጥናት ተካሂዷል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮና የኤጀንሲ ኃላፊዎች፣ የድጋፍ ባለሙያዎች እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣ ግሎባል ፈንድ የኢትዮጵያ መንግስት የጤናውን ስርዓት በማጠናከር በተለይም የኤች አይ ቪ፣ የወባ እና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚተገበሩ ስራዎች ላይ ለሚያከናውናቸው የድጋፍ ተግባራት እና ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ከግሎባል ፈንድ በተገኙ ድጋፎች የኤች አይ ቪ፣ የወባ እና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን እና ህመምና ሞት በመቀነስ በኩል ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው በቀጣይ የተገኙ ውጤቶችን ለማስፋፋትና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ስራዎችን መተግበር እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ በቀጣይ የ 440 ሚልዮን ፕሮጀክቶች ትግበራን በፍጥነት ለመጀመር የሚያስችል አቅጣጫ ላይ በመወያየት ከክልሎች፣ ኤጀንሲዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል። ባለፈው የግራንት አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘጉቡ ተቋማት እና የስራ ክፍሎች የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።