በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ሳምንት ከመቶ ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የነጻ የጤና ምርመራ እና ህክምና አገልግለት ለመስጠት የተጀመረው ሰው- ተኮር የበጎ ፈቃድ የተግባር ዘመቻ በሁሉም ክልሎችና በከተማ መስተዳደሮች በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል፡፡
በዘመቻውም የጤና አጠባበቅ ትምህርትና ምክር አገልግሎት ፣ በተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ፣የኮሌራና ሌሎች ውሀ ወለድ በሽታዎች፣ ወባ፣ ኤች አይ ቪ ፣ ቲቪ ፣ ኮቪድ-19፣ የካንሰር ህመምና ሌሎች ትኩረት በሚሹ የጤና ጉዳዮች ላይ ማለትም የደም ግፊት ፣የደም የስኳር መጠን፣ ከአንገት በላይ፣ የአይን፣ የቆዳ፣የስነ ምግብ፣ የአእምሮ ጤና እና ሌሎች የጤና አገልግሎቶች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በተለይም የችግኝ ተከላ፣ የከተማ ግብርና የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማደስ እና ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቀሶችን መደገፍ የመሳሰሉትን ስራዎች በመስራት የመረዳዳት ባህላችንን በማጎልበት ላይ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል፡፡